Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

» » » የሕይወት መርህ (ሚካኤል ዲኖ)


ሕይወታችን ቢቃወስ ፤ ያልጠበቅነውና ያላሠብነው ክስተት ቤታችን ቢገባ፤ ዓላማችንና ራዕያችን የሚበጠብጥ ጋሬጣ ከፊታችን ቢደቀን አንደንግጥ፤ እጅ አንስጥ። የሕይወት መንገድ አዳላጭ፣ የሠው ባህሪ ተንሸራታች፣ የዓለም ፀባይ ተገለባባጭ መሆኑን ተረድተን ሕይወት ቢያዳልጠንም፣ ሠው ቢንሸራተትብንም፣ ዓለም ቢገለባበጥብንም አኛነታችንን አንርሣ፡፡ አወዳደቃችን እንዲያምር ስንወድቅ ውስጣዊ ማንነታችን አይውደቅ ፡፡ ስንነሣም አቋማችንን ይዘን እንነሣ፡፡ ተስፋችንን ዘወትር ነፍስ እንዝራባት፡፡ ለራሳችን አለሁ እንበል! ብወድቅም እነሳለሁ እያልን ለውስጣችን እንንገረው ፡፡
ነገሮች የተከረቸሙብን ቢመስሉም መክፈቻ ቁልፉ ግን ከእጃችን አለ፡፡ እኛነታችን ሊመዘን ፤ ማንነታችን ሊታይ ሲል ፈተናዎች ሊከቡን ይችላሉ ፡፡ ፈተናዎችን በድል ለማሸነፍ ረጋ ብለን ነገሮችን አናስተውል ፡፡ የመጣው ነገር ሊፈትነን ብቻ ሳይሆን መልካም ነገርም አጠገቡ ይዞ ነው ፡፡ ክፉውን በመልካም ፤ ስጋቱን በዕድል መለወጥ እንድንችል ውስጣችን አይደንግጥ ፡፡ ማንነታችን አይረበሽ ፡፡ የምናጣቸው ነገሮች ያሉ ቢሆንም የምናገኛቸው ነገሮች ሊልቁ ስለሚችሉ ስለወደፊታችን በቀናነትና በበጎነት ነገሮችን እንመልከታቸው ፡፡ የነገሮችን አመጣጥና አከዋወን ፍሬ ነገራቸውን አናጥና፡፡
የምንችለውን እና የአቅማችንን አናድርግ። ከችግራችን ጋር ኑሮን ተሟግተን ማሸነፍ ካልቻልን፤ ወድቀን፣ ተነስተን፣ ተፍጨርጭረን ካልሆነልን አሁንም አምላካችንን እንጥራ፡፡ አምላኬ ተናገረኝ እንበለው፡፡ በፀሎታችን እንትጋ፤ የችግሬን ሠንኮፍ ነቅለህ ሕይወቴን አድስ እንበለው፤ ችሎታውንና ጥበቡን አድለኝ እንበለው፤ አቅሜ አለቀ፣ ሀይሌ ተሟጠጠ እንበለው ያን ጊዜ ሐያሉ አምላክ ከችግራችን ያላቅቀናል፤ መሠናክሉን ያሻግረናል፤ ቋጠሮውን ይፈታልናል፤ ውስብስቡን አቅልሎ ሕይወታችንን ያድስልናል፤ ጥበቡንና ችሎታውን፤ መላውንና መንገዱን ያሣየናል፤ አቅሙንና ሃይሉን ይፈጥርልናል፤ የጌቶች ጌታ፣ የነገስታት ንጉስ፣ የዓለም ፈጣሪ ዓላማችንን ያስተካክልልናል።

«
Next
Newer Post
»
Previous
Older Post

No comments:

Leave a Reply