Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

» » » ፍቅር ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው።


መልካም ነገርን ለመስራት ሃይማኖተኛ ወይም መማር አልያም ልዩ መሆንን አይጠይቅም፤ ብቸኛው መመዛኛ ሰው መሆን ብቻ ነው። መልካም ነገርን ማድረግ ባንችል እንኳን በሰው ላይ ጥፋት ሳይሰሩ ለመኖር የሚያስችል ህሊና ሊኖረን ይገባል።

ብዙዎች ጥላቻን በጥላቻ፤ የታሪክን ስህተት ደግሞ በበቀል ሊያጠፉ ደፋ ቀና ሲሉ እናያለን ይህ ግን ሞኝነት ነው ምክንያቱም ማንም ሰው በጥላቻ እና በክፋት ፍሬ ያፈራ የለምና።

በአንድ ወቅት የነጻነቱ ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ
"…ማንም ሰው ሌላውን ሰው በዘሩ እና በቆዳው ቀለም፤ ወይም በሃይማኖቱ እንዲጠላ ሆኖ አልተወለደም፤ ሰዎች
መጥላትን ተምረውት ነው። የሰው ልጅ ጥላቻን ከተማረ፤ ፍቅርንም መማር ይችላል፤ እንደውም ፍቅር ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው።”
ብሎ ነበር። እውነትም ነው በጥላቻ ግዜያችንን ከማጥፋት ይልቅ በፍቅር እና ስምምነት ብዙ ነገሮችን መለወጥ እንችላለን። ፍቅርን መማር ጥላቻን ከመማር በላይ ይቀላልና ፊታችንን ወደ ፍቅር እንመልስ ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን!!

«
Next
Newer Post
»
Previous
Older Post

No comments:

Leave a Reply