Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ - [ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው]

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በዚህ መልክ አብን ቢሮ ይገኛሉ። ወጣቶቹ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ፍትህ እናገኛለን ብለው ነበር።  


ሆኖም የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የአብንን ቢሮ ከብቦ ወጥተው አቤቱታቸውን እንዳያሰሙ አግዷቸዋል። "ከወጡ እንተኩሳለን" እያለ መዛቱ ተገልፆአል።

ለወጣቶቹ ተራ ጀሮ ጠቢና ፖሊስ መላኩ አይደለም የሚገርመው። አንድ ከሰራዊቱ የወጣና በየጋዜጣው "ሪፎርም ያስፈልጋል" ሲል የምናውቀው ጀኔራልም ሁኔታውን ለማየት በቢሮው በኩል ሲያልፍ ተመልከቻለሁ። እንግዲህ የትህነግን ሰላዮች ስምሪት የሚቆጣጠረውና ወደ መቀሌ ሪፖርት የሚያጠናቅረው ይህ ጀኔራል ይሆናል።
ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ
ወልቃይት ጠገዴ 1983 ዓ.ም በትግራይ መንግስት በኃይል መያዙ ይታወሳል፡፡ የትግራይ መንግስት ወልቃይት ጠገዴ የማንንት ጥያቄ ባቀረቡ የወልቃይት አማራዎች ላይ አስር፤ሰቆቃ፣ ግድያ ሲፈፀም ቆይቷል፡፡

የትግራይ መንግስት አማራዎችን በማፈናቀል በአንፃሩ የህዝቡን ስብጠር ለመቀየር ትግሬዎችን ከአድዋ፣ ከአድግራት፣ ከአንደርታ፣ ከአክሱም… ወዘተ በማምጣት በወልቃይት ለም መሬቶች ላይ አስፍሯል፡፡

በአካባቢው የትግራይ መንግስት በዘረጋው የአፈና መዋቅር የወልቃይት ጠገዴ አማራ ተወላጅ ላይ የተጠና አስተዳደራዊ በደል እየፈፀመ ይገኛል፡፡ ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴርም እየተፈፀመ ያለውን በደል እንዲረዳና አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን የሚከተሉትን ዋና ዋና ጥያቀዎቻችን እናቀርባለን፡፡

  • የትግራይ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ አማራ ላይ የሚፈፅመውን ግድያ፣ አፈና፣ሰቆቃ፣አስር እና መፈናቀል በአስቸኳይ እንዲያቆም 
  • የወልቃይት ጠገዴ አማራዋች በቋንቋችን በአማርኛ የመናገር የመማር የመፃፍ፤በበህላችን ሀዘንና ደስታችን የመግለፅ መብታችን አንዲከበር
  • በትግራይ መንግስት የሚፈፀም የመሬት ዝርፊያ እንዲቆምልን እና ሐብት ንብረት የማፍራት መብታችን እንዲረጋገጥ
  • በማንነታቸው ምክንያት ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው ሶሮቃ ጎንደር አዲስ አበባ በጊዚያዊ መጠለያ የሚገኝ የወልቃይት ጠገዴ አማራዎች በአስቸኳይ ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱና የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ እንዲደረግ

  • ትግራይ ፀጥታ አካላት ወልቃይት ጠገዴን ለቀው እንዲወጡ እና የፌደርል የፀጥታ አካላት በቦታው እንዲተኩ እንዲደረግ
  • የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማነንነት ጥያቄ በአስቸኳይ እንዲመለስ 
  • ወደ ወልቃይት ጠገዴ የመጡ የትግራይ ሰፋሪዎች በማንነታችን ጥያቄ ላይ የሚፈፅሙትን ሴራና ደባ እንዲቆሙልን
ለወጣቶቹ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ አራት ኪሎ ግንፍሌ ከድልድዩ ወደ ጃንሜዳ በሚወስደው መንገድ በኩል የሚገኘው የአብን ቢሮ በመሄድ ማገዝ ትችላላችሁ።
ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ

ኢሳያስ ለምንና ለማን መጣ? (ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው)



ኢሳያስ ለምንና ለማን መጣ?

ከእንቅልፌ ነቅቼ ወደ ፌስቡክ ሰፈር ሳቀና "ኢሱ! ኢሱ" የሚል የፌስቡክ ጩኸት ይሰማኛል። ኢሳያስ ወደ አዲስ አበባ መጣ ብለው የሚደሰቱ ወገኖችን ፅሁፍ አነበብኩ።  


ብዙዎቹ ኢሳያስ የሰላም ስምምነት ሊፈራረም እንደመጣ ይገልፃሉ። የአሰብም ጉዳይ አብሮ ይነሳል። ጥሩ ነበር። አብይ ወደኤርትራ ሁለት ጊዜ አቅንቷል። ኢሳያስ ከሁለት ወር በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ነበር። በመሃል ከአብይ ጋር መካከለኛው ምስራቅ ተገናኝተው ተነጋግረዋል። 

እንደእውነቱ መሪዎቹ ከአራት ጊዜ በላይ የተነጋገሩበትን ባለሙያዎች ይሰሩታል። ኢሳያስ ለስራ ጉብኝት ወደ አዲስ አበባ መጣ የሚባለው ለሰላም ስምምነቱ አይመስለኝም። በእርግጥ የሆነ ወረቀት ላይ ሊፈራረሙ ይችላሉ ይሆናል።

ኢሳያስ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበት ዋናው ምክንያት የሚሆነው የዳውድ ኢብሳ ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት ዳውድ ኢብሳ በእነ አብይ "አንደኛ ደረጃ በጥባጭ" ተብሎ ተፈርጇል። ዳውድ ኢብሳ "ጦርነት ከፈለጉ" ሲላቸው እነ ዶክተር አብይ "የአፍ ወለምታ ይሆናል" ሲሉ የሰነበቱት ሰውየውን ስለፈሩት ነው። 

በዚህ ወቅት ቄሮን "ተነስ" ብለው እነ አብይን ማስጨነቅ የሚችሉት ዳውድ እና ጃዋር ናቸው። እነ ዳውድ ቄሮውን በለማ ላይ ዝመት ቢሉት ይዘምታል። ዳውድ ቄሮን ተማምኖ እንጅ ከ700 የማይበልጥ ጦሩ ሊያድነው አይደለም።

እነ አብይ አህመድ ዳውድን ሲለማመጡ ብዙ ድጋፋቸውን አጥተዋል። ኦዴፓ (ኦህዴድ) ኦሮሚያ ውስጥ አቅመ ቢስ ሆኗል። እነ አዲሱ አረጋ፣ እነ ታዬ ደንዳአ በኦሮምኛ ሲያባብሉ የሚውሉት ዳውድ ስላስቸገራቸው ነው። 

 በዚህ ሂደት እነ አብይ ከኦህዴድ ጀምሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትዝብት ውስጥ ገብተዋል። ዳውድ እያቅራራባቸው እነሱ እየተለማመጡ ነው። ሌሎቹን ትጥቅ አስፈትተው ዳውድ ግን ከፈለጋችሁ ግጠሙኝ እያላቸው ነው።

ኦዴፓ በዳውድ ላይ ብዙ ሰው አዝምቷል። የቀድሞው የኦነግ መሪ ሌንጮ ለታ በይፋ በሚዲያ ተችቶታል። ለሌንጮ ኦዴፓ ዋስትና ስለሚሆነው እንጅ ሌላ መጠጊያ የለውም። ጀኔራል ከማል ገልቹ ከዳውድ አንፃር ሲታይ ለዘብተኛ ብሄርተኛ ነው። የኦነግ አንደኛው መሪ ከማል ነበር። 

ሌንጮ፣ ዳውድና ከማል ኦነግን ለሶስት ሸንሽነውት ነበር። ሶስቱ መሪዎች አይንና ናጫ ከሆኑ ቆይተዋል። ከማል የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ጉዳይ ኃላፊ ተደርጎ መሾሙ ተገልፆአል። ይህም ሌላ በዳውድ ላይ የተደረገ ዘመቻ ነው። ይህም ግን ዳውድን አላንበረከከውም። ቄሮ ማንን በደንብ እንደተቀበለ እና እንደሚቀበል ሁሉም ገብቷቸዋል። በተለይ ዳውድ ተማምኖበታል። እነ አብይም ዳውድን ደፍረው መናገር አልቻሉም። ዳውድን ደፍሮ መናገር የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው። ኢሳያስ አፈወርቂ!

ዳውድ ኢብሳ ለረዥም ጊዜ አስመራ ውስጥ ኖሯል። ዳውድ ባለው ጠርዝ የያዘ አመለካከት ከኢሳያስ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸው ይነገራል። ከሶስቱ የኦነግ መሪዎች አስመራ በቅንጦት ይኖር የነበረው ዳውድ ነበር። በኢሳያስ የተመረጠው ዳውድ ኢብሳ ነው። ጀኔራል ከማል ገልቹ እና ሌንጮ ለታ ተንከልክለው ሲገቡ ዳውድ አስመራ ላይ ቀብረር ብሎ የቆየው እንዲሁ አይደለም።  

የኢሳያስ ድጋፍ ስላለው ነው። እነ ግንቦት ሰባት ያለ በቂ ድርድር የገቡት ነገ ኢሳያስ "ውጡ" ቢል አማራጭ ስለሌለ ነው። ዳውድ ግን ኢሳያስ እንደማይቆርጥበት ስላወቀ ለማ መገርሳን ኤርትራ ድረስ አከላትሞታል። አቅሙንም ለማሳየት ጭምር ነው። መለማመጡ በከፋ ሁኔታ የጀመረው ያኔ ነው።

ዋናው ከኢሳያስ ጋር ፍቅር መሆናቸው ብቻ አይደለም። ዳውድ ኢሳያስን መስማቱ ብቻ አይደለም። ኤርትራ ውስጥ ሲኖር የቤተሰብና ሌሎች መረጃዎቹ ሳይቀር ከኤርትራ ደሕንነቶች እይታ አያመልጡም። ኢሳያስ በቀድሞው ጊዜ ቢወደው፣ በጣም ሲተብት "አርፈህ ተቀመጥ" የሚያሰኝ መረጃ አለው።  

ለሁለት አስርት አመት ኤርትራ ውስጥ የነበር ሸማቂ ጦሩ ተራራ ወጥቶ፣ ወርዶ (ስልጠና) ተኝቶ ከመዋል ውጭ "ኦፕሬሽን" የሚያደርገው ከስንት አንድ ጊዜ ነው። ቀሪው ጊዜ የእረፍት ነው። በተለይ ለመሪዎች ሰፊ ጊዜ ነበራቸው። በዚህ የእረፍት ጊዜ እነ ዳውድ ንግድን ጨምሮ ብዙ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ግልፅ ነው። በአንዳንዶቹ ላይ መረጃዎች አሉ። 

ከዚህ የከፉም መረጃዎች ይኖራሉ። ይነገራሉም። ይህ ለኢሳያስ አቅም ነው። ኢሳያስ ወደ አዲስ አበባ የመጣው "እባክህ ዳውድን ተቆጣው" ተብሎ ይመስላል። እነ አብይ ትግስታቸው እያለቀ ይመስላል። ችግር ከመፈጠሩ በፊት፣ ኦሮሚያ ውስጥ ችግር ከመፍጠሩ በፊት አንድ በልልን ተብሎ ነው።

በእርግጠኝነት ለማስመሰል የሆነች ወረቀት ላይ ውል እየተዋዋሉ ያሳዩናል። በሚዲያም የስምምነት ዝርዝር ይነግሩን ይሆናል። የሰላም ስምምነት ሊሏትም ይችላሉ።  

ምን አልባት ለዳወድ ጉዳይ መጥቶ ጨርሶት የሚሄድ ጉዳይም ሊኖረው ይችላል። ተዋዋልን ቢሉ እንኳ በውስጥ ቀስ እያሉ የሚጨርሷት ጉዳይ ትኖራለች እንጅ ቅድሚያው ዳውድ ኢብሳ ነው!