Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

ርግማን ሃራም ነው! (አሌክስ አብርሃም)

ርግማን ሃራም ነው! (አሌክስ አብርሃም)

ርግማን ሃራም ነው! 
(አሌክስ አብርሃም)


ሙልቅቅ
እፍፍፍፍፍስ
ጥርርርርርርርግ
ሙጥጥጥጥጥጥጥጥ
ምጥጥጥጥጥጥጥጥ


አድርጋችሁ ባዶ የድንጋይ ከምር እንደሰጣችሁን
ቋጥኝ ይናድበት ርኩስ ሃብታችሁን !
ለወሬ ነጋሪ ስማችሁ አይትረፍ
የዘመን ጨለማ በቤታችሁ ይግዘፍ
የዘረፋችሁት የደሃ አገር ጥሪት
አውሎ ነፋስ ይሁን ይብላችሁ አዙሪት !

ብየ እንዳረግማችሁ ርግማን ሃራም ነው!
ት . . . ክን !
እርርርርርርር!
ድብ. . . . ን አርጋችሁን እንደከረማችሁ
በረከት ይራቀው ደም አፍሳሽ እጃችሁ
ጸሃይ አይውጣበት ጨለማ ነፍሳችሁ

ሃይል አመንጩ ብለን በሰጠነው ጥሪት
እንዳመነጫችሁ ሃፍረትና ውርደት
የዝርፊያ ሃብታችሁ እሳት ይውረድበት !
አገሬው ላገሩ እንደሆነ እንግዳ
ተወላጅ በምድሩ እንደሆነ ባዳ
የግራችሁ ማረፊያ ምድር ትራቃችሁ
ተቅበዥባዥ ምንደኛ ሁኑ በደጃችሁ

ብየ እንዳረግማችሁ ርግማን ሃራም ነው !
እንደሲኦል ጉድጓድ ከርሳችሁ ላይሞላ
ጨካኝ መንጋጋችሁ የሚስኪኖች ተስፋ ጨክኖ እንደበላ
አባልቶ ይፍጃጅሁ አላሁ ተአላ !

ብየ እንዳረግማችሁ ርግማን ሃራም ነው !!
ብቻ
ህግ ይላክባችሁ ለጃችሁ ካቴና
ለዘረፋችሁት ያገር ባዶ ካዝና
ላስለቀሳችሁት የሚራራ እንባ አባሽ
ላሳመጻችሁት ጥሩ ፈጥኖ ደራሽ 

ይረፍና እንየው እግራችሁ ፍርድ ቤት
ጎናችሁ ከርቸሌ
አላሁ መሶሌ !!

ኢሳት ዜና– መስከረም 5/2010

የኬንያ ፍርድ ቤት ወደ ሀገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል ያላቸው 40 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ሲል ውሳኔ አሳለፈ። ፍርድ ቤቱ ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው ከመመለሳቸው በፊትም የአንድ ወር እስራትና እያንዳንዳቸው 20 ሺ ሽልንግ እንዲቀጡም ወስኗል።
አብዛኞቹ እድሜያቸው በ20ዎቹ አጋማሽ ላይ እንደሆነ የተገለጸው ኢትዮጵያውያን ወደ ኬንያ በህገወጥ መንገድ የገቡት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሸጋገር ነው በሚል ፍርድ ቤቱ ያቀረበባቸውን ክስ አምነዋል።
40ዎቹ ኢትዮጵያውያን የሚከራከርላቸው ወይንም ዜጎቼ ብሎ ስለመብታቸው የሚቆምላቸው መንግስት ባይኖርም ራሳቸው ግን ፍርድ ቤቱ ያሳለፈባቸውን ውሳኔ እንዲቀይርላቸውና ይቅርታ እንዲያደርግላቸው እምባቸውን በማፍሰስ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ የተወሰነባቸውን የገንዘብ ቅጣትንም ቢሆን ስራ ስለሌላቸው መክፈል እንደማይችሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። –ፍርድ ቤቱ ለጥያቄያቸው ምን መልስ እንደሰጠ ባይታወቅም እንኳ።
በፍርድቤቱ የቀረቡት 67 ኢትዮጵያውያን ቢሆኑም 27ቱ ግን ወደ ሀገሪቱ በህገወጥ መንገድ አልገባንም ሱሉ በመከራከራቸው ጉዳያቸው በይደር ተይዟል። ወደ ሀገሪቱ ሲገቡ ገንዘባቸውንም ሆነ ፓስፖርታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ ማስረጃቸውን የፖሊስ ሃላፊዎቹ ወስደውብናል የሚል የመከራከሪያ ነጥብም አቅርበዋል። ዳኛው የ27ቱ ኢትዮጵያን ጉዳይ እስከሚጣራም በጊጊሪ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ትእዛዝ ሰጥተዋል።መረጃውን ያገኘንው ከኬንያ የዜና አውታር ነው።

ይፈታል - ከእሸቱ ታደሰ


ይፈታል!

ከእሸቱ ታደሰ

ህልማችን ይፈታል ቅርብ ነው ድላችን
ጌታም በቃ ይላል ይመልሳል ፊቱን
ግና ዋናው ነገር ከኛ ሚጠበቀው
ያገራችን ክብር ዳግም የሚፀናው
የኛን መገፋፋት ከኋላ ጥለነው
ዘረኝነትና ጎጠኝነት ጠፍተው
ከልዩነት በላይ ባንድነት ስንሆን ነው።

ከእሸቱ ታደሰ (Eshe Man Tade)

አለ አንድ ነገር! (እሸቱ ታደሰ)


  አለ አንድ ነገር!

(ከእሸቱ ታደሰ)

በሆነ ባልሆነው ህዝብን ከነካኩት
እሺ ይሁን ብሎ ችሎ ተሸክሞት
ይኖር ይኖርና ጊዜ እስኪመጣለት
አንድ ቀን ሲበቃው እምቢኝ ያለ ለታ
ግፉ ከጫፍ ደርሶ ሲበዛ ኡኡታ
ማንም አያቆመው እኔ ነኝ ያለ ወንድ
ያንቀጠቅጠዋል የትም ሸሽቶ ቢሄድ
ይኸው ተጀምሯል ባንድነት ትብብር
ቀኑ ተለውጧል አለ አንድ ነገር
ወኔ መች ጠፋና ከአምቦና ጎንደር

ከእሸቱ ታደሰ (Eshe Man Tade) - 

ፍትህ ለእማዋይሽ (እሸቱ ታደሰ)


ያገር እድገት ከጫፍ ደርሶ፥
ችግር ስቃይ ተገርስሶ፥
ወገን ደስታ ሳይለየው፥
ፍቅር ሰላም ውስጡን ሞልተው፥
በነፃነት ይኖሩ ዘንድ ተመኝተሽ፥
ፍትህን ለማስፈን ዘብ ብትሆኚ ለወገንሽ፥
ያለጥፋት ያለበደልሽ፣
በፍርደ-ገምድል በግፍ አሰሩሽ።
ያንን ሁሉ ህመም ስቃይና እስራት፥
ተቋቁመሽ ችለሽ በተስፋና ፅናት፥
ላገር ብለሽ ለእኛ ብለሽ እንዳንጠፋ እንደዋዛ፥
እራስሽን አሳልፈሽ ለሰጠሽን ሕይወት ቤዛ፥
ጎንበስ ብለን ካንገታችን፥
ሰበር ብለን ከወገባችን፥
አክብረናል ለፀናሽው ለክብራችን፥
እድሜን ይስጥሽ ከጤና ጋር እማዋይሽ እናታችን።

ህልማችን ይፈታል


ህልማችን ይፈታል ቅርብ ነው ድላችን
ጌታም በቃ ይላል ይመልሳል ፊቱን
ግና ዋናው ነገር ከኛ ሚጠበቀው
ያገራችን ክብር ዳግም የሚፀናው
የኛን መገፋፋት ከኋላ ጥለነው
ዘረኝነትና ጎጠኝነት ጠፍተው
ከልዩነት በላይ ባንድነት ስንሆን ነው።

ከእሸቱ ታደሰ (Eshe Man Tade)

አንድ ነገር አለ (እሸቱ ታደሰ)

በሆነ ባልሆነው ህዝብን ከነካኩት
እሺ ይሁን ብሎ ችሎ ተሸክሞት
ይኖር ይኖርና ጊዜ እስኪመጣለት
አንድ ቀን ሲበቃው እምቢኝ ያለ ለታ
ግፉ ከጫፍ ደርሶ ሲበዛ ኡኡታ
ማንም አያቆመው እኔ ነኝ ያለ ወንድ
ያንቀጠቅጠዋል የትም ሸሽቶ ቢሄድ
ይኸው ተጀምሯል ባንድነት ትብብር
ቀኑ ተለውጧል አለ አንድ ነገር
ወኔ መች ጠፋና ከአምቦና ጎንደር

በአንድነት አንድ እንሁን!!! (እሸቱ ታደሰ)


በዚህች አለም ለሁሉም ፍጡራን በቂ የሆነ ስፍራ አለ። ምድሪቱ ባለፀጋ ነች ለሁላችንም ትተርፋለች። አኗኗራችን ነፃና ውብ መሆን ይችላል ግን መንገዳችንን ሳትን፤ ስስት የሰውን ልብ መረዘ፤ አለምን በጥላቻ ከፋፈለ፤ ምኞት ደም መፋሰስ ውስጥ ከተተን። በፍጥነት መጓዝ ብንችልም በራሳችን ውስጥ ተቀብረናል፤ ብዙ መስጠት የሚቻለው ጥበባችን ፈላጊዎች አድርጎናል፤ እውቀታችን ተጠራጣሪ፣ ጉብዝናችን ጨካኝና ክፉ አድርጎናል፤ ብዙ አሳቢዎች ግን ስሜት አልባዎች ሆነናል።

በአሁን ጊዜ ከማሽን ይበልጥ ሰብዓዊነት፤ ከጉብዝና ይልቅ ደግነትና ሩህሩነት ያስፈልገናል። ያለነዚህ ብቃቶች ህይወት ቀውስ ውስጥ ትሆንና ሁሉንም እናጣለን።

በአሁኑ ጊዜ ሚሊየን ተስፋ ያጡ ወንዶች፣ ሴቶች፣ ህፃናትና የእድሜ ባለፀጎች በሚያሰቃይና ንፁሃንን በሚያስር ስርዓት ተጠቂዎች ናቸው።

ለእናንተ ይህን ለምታነቡት እላችኋለሁ… ተስፋ እንዳትቆርጡ፤ የወረደብን መከራ ምንም አይደለም የሚያልፍ ስስት ነው፤ የሰው ልጅን እድገት የሚፈሩ ሰዎች ጭካኔ ነው፤ የሰዎች ጥላቻ ያልፋል፤ አምባገነኖችም ይሞታሉ፤ የወሰዱት ስልጣን ለህዝቡ ይመለሳል፤ እስከሞትንላት ድረስ ነፃነት መቼም አትቀርም።

ወታደሮች ሆይ እራሳችሁን ለጨካኞች አትሰው። ለሚያንቋሽሿችሁ፣ ባሪያ ላረጓችሁ፣ ህይወታችሁን ለሚመሩ፣ ምን እንድታስቡ፥ ምን እንዲሰማችሁ ለሚነግሯችሁ፣ ለሚበያራቁቷችሁ፣ እንደ ከብት ለሚነዷችሁ፣ ጥይት ለሚቀልቧችሁ፣ ለእነዚህ ሰዎች አትሰዉ!! የሰው ማሽኖች፤ መሳሪያ እራሶች፤ መሳሪያ ልቦች አይደላችሁም… ከብት አይደላችሁም… እናንተ ሰው ናችሁ… የሰብዓዊነት ፍቅር በእናንተ ውስጥ አለ… አትጥሉ! ፍቅር ያጡና ተፈጥሮ የሌላቸው ብቻ ናቸው የሚጠሉ።

ጓዶች…ለባርነት አትዋጉ ለነፃነት እንጂ። ቅዱስ ማርቆስ እንዳለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሰውነታችሁ ነው፤ በአንድ ሰው አይደለም፣ በቡድን አይደለም፣ በሁሉም ሰው… በእናንተ ውስጥ ነው። ሀይል የህዝብ ነው፤ መሳሪያ የመፍጠር፤ ደስታን የመፍጠር፤ ይህንን ህይወት ነፃ፣ ውብና የተሻለ የማድረግ ሀይል አላቹ። በዲሞክራሲ ስም ይህንን ሀይል እንጠቀምበት፤ በአንድነት አንድ እንሁን፤ ቅድስት ለሆነች ሃገራችን እንታገል።

ቀና ለሆነው ህዝባችን ቀና ለመሆን፤ የመስራት እድልን ለሁሉም ዜጋ ለመፍጠር፤ ለወጣቱ መፃኢ ተስፋ ለመቆም ቃል በመግባት ነው ጨካኞች ስልጣን ላይ የሚወጡት! ግን ዋሽተውናል፤ ቃላቸውን አልጠበቁም መቼም አይጠብቁም። አምባገነኖች ራሳቸውን ነፃ ያወጣሉ ህዝቡን ግን ባርያ ያደርጉታል። ቃላቸውን አፍርሰዋልና ያንን ቃል እኛው በእኛው ለማስፈፀም እንታገል፤ ሃገራችንን ነፃ ለማውጣት፤ ድንበራችንን ለማስከበር እንታገል፤ ስስትን
ለመጣል፣ ጥላቻንና አለመቻቻልን ለማስቀረት፣ በምክንያት ለተፈጠረች ሃገራችን ስንል እንታገል።

ጓዶች ስለነፃነት፣ ፍትህ፣ ሰላም፣ እኩልነትና ከምንም በላይ ስለቅዲስቷ ሃገራችን ስንል በአንድነት አንድ እንሁን።