የሀገራችን ጥበበኛ ዛፍ ቆራጮች ከርዝመቱ፣ ከውፍረቱ፣ ካዳገበት ቦታ ጠባብነትና ከቅርንጫፎቹ ብዛት የሚያስፈራውን ዛፍ አንድም ጉዳት ሳያደርስ ያጋድሙታል። የአቆራረጥ ጥበባቸውን ላስተዋለ በቅድሚያ ዛፉንና ዙሪያውን በደንብ ያጠናሉ፤ ከዚያም ከአናት ይወጡና ተራ በተራ ቅርንጫፎቹን በመመልመልና ግንዱን ለመጣል ያላቸውን ቦታ በመገመት ከላይ ጀምረው በመጠን በመጠን እየቆረጡ ካሳነሱት በኋላ አካባቢው ላይ ጉዳት ሳያደርስ ከስሩ ቆርጠው ይጥሉታል።
የፖለቲካውም ትግል በዚህ ስልት መካሄድ ያለበት ይመስለኛል፡፡ በቀጥታ ግንዱ ላይ አተኩሮ የሚደረግ ትግል ጉዳቱ ያመዝናል። አደጋውን ለመቀንስ፣ መስዋዕትነቱን ለማሳነስና ውጤቱንም አስተማማኝና ዘላቂ ለማድረግ ግንዱንና ቅርንጫፎቹን ለይቶ ማወቅ፤ የቅርንጫፎቹን ብዛት፣ ውፍረትና ርዝመት በማጤን እቅድ አውጥቶና የአፈጻጸም ስልት ነድፎ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።
ግንዱ መውደቁ አይቀርም፤ በመውደቁ ግን አካባቢው ላይ የከፋ አደጋ እንዳያደርስ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል።
የፅሁፍ ሃሳብ - ይገረም አለሙ
No comments: