በዓለማችን ላይ ስለ ዘለዓለማዊ ደስታ ሲሉ ጊዜያዊ ደስታን መስዋዕት ያደረጉ፤ በመልካም ሥራቸው የምናደንቃቸውና የምናከብራቸው፤ መልካም ምግባራቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የተለያዩ ግለስቦች አሉ። በሃገራችንም ለተቸገሩ ወገኖች በመድረስ ከሁሉም በላይ የህሊና እርካታና ውስጣዊ ደስታን የተጎናፀፉ፤ መልካምና የተቀደሰ ሥራን እየሠሩ ያሉ በርካታ ግለሰቦች አሉን።
ቢንያም በለጠ ይባላል በጎነትና ቅንነትን በማስቀደም ለወገኑ እራሱን መስጠት የሱነቱ መገለጫዎች ናቸው። ቢንያም ከሚኖርበት አሜሪካ ወደ እናት ሃገሩ በመመለስ
መቀዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ድርጅትን በማቋቋም ለወገኑ ያለውን ፍቅር በተግባር ያሳየ የዘመናችን በጎ ሰው፤ እራስወዳድነት በነገሰበት በዚህ ዘመን ጉልበትና እውቀቱን መስዋዕት በማድረግ፤ ገንዘቡን ሳይሰስትና ደከመኝ ስለችኝ ሳይል አቅሙን አሟጦ ለወገን ደጀን መሆኑን በተግባር ያሳየን ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው።
በበጎነት አስተሳሰብ ለታነፀ አዕምሮ መልካምነት ከሁሉም በላይ በሰው ልጅ የዕለት ተለት የኑሮ መስተጋብር ሊንፀባርቅ የሚገባው አብይ ጉዳይ በመሆኑ ወገኖቻችንን ለማገዝና የቢኒን መልካም ተግባር ለመደገፍ ሁላችንም ከጎኑ ልንቆም ይገባል እላለው።
"ሰውን ለለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው"
ክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ
No comments: