Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

» »Unlabelled » ይድረስ ስለኢትዮጵያና ህዝባችን ዘላቂ መፍትሄ ለምንሻ ወገኖች በሙሉ - (ግርማ በቀለ)


የምንጽፈው፣ ቀድሞ የጻፍነውን ደግመን የምናጋራው/ሼር የምናደርገው/ የምንሰጠው መረጃና የምናቀርበው ማስረጃ ለለውጥ ትግሉ ግብዓት እንዲሆን እንጂ- ማንንም ለማስደሰት ወይም ይህን ‹‹ብለን ነበር›› ለማለት፣ አሊያም የተለየ የግል ዓላማም ፍላጎትም ስላለን አይደለምና---እባካችሁ በምንጽፈው/በምናሰራጨው መልዕክት ሁሉ ከዘረኝነት በጸዳ፣ ልዩነትን በማይለጥጥና በማያሰፋ መንገድ ፣ የለውጥ ትግሉን ማዕከል አድርገን እንወያይ፡፡ የግልና የቡድን ፍላጎቶችን በአገርና የህዝብ ጉዳዮች ላይ ለመጫን መባተት ማናችንም አይጠቅመንም፡፡ በየቱም ቦታ፣ጊዜና ሁኔታ በማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚደርሰው ኢሰብዐዊና ህገወጥ በደል፡-- ግድያ፣ ሃብት-ነጠቃና ማፈናቀል፣ጥቃት… .በእኩል ይመመን፤ ያለልዩነት--ከትግራይ እስከ ደቡብ ኦሞና ሞያሌ፣ ከጋምቤላና ቤኒሻንጉል እስከ ኦጋዴንና አፋር፡፡
ዘረኝነትን ተከትሎ የሚመጣው ሰደድ-እሳት ማናችንም አይምርም፤ይህን ለመረዳት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዛሬ በተጨባጭ በዓይናችን እያየን ነው፡፡ከነዚህ ወቅታዊ ሁኔታዎች በአማራ-ትግራይ ድንበር ያለው ውጥረት፣ በኦሮሚያ-ኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች የተለያዩ ድንበር አካባቢዎች የመንግስት ታጣቂዎች የተሳተፉበት ግጭትና ያስከተለው የህይወት መጥፋትና የዜጎች መፈናቀልና ሥቃይ፣ በሃረሪ ክልል በሀረሪ ሊግና ኦህዴድ ባለሥልጣናት መካከል የተፈጠረው ትርምስ፣ በደቡብ (ሲዳማ፣ኮ ሬ፣ አማሮ) እና ኦሮሚያ (ጉጂ) ድንበር አካባቢዎች፣ በደቡብ ክልል በሲዳማና ዎላይታ ድንበር አካባቢ የተፈጠረው ውጥረት፣….በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ከሚሰማው የህዝብ ብሶት በተጨማሪ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል እየገዘፈ የመጣው ልዩነትና ያለመተማመን የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በጠቅላይ ሚ/ሩ የተቀመጠው ‹‹ዋና--ዋና መንገዶች ለፌደራል ኃይል መሰጠት›› እንደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ‹‹በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ብቻም ሳይሆን የኮንትሮባንድ መስመሩን የመቆጣጠርና ክልሎች የሚያደርጉትን ጥብቅ ፍተሻ ማስቀረትና ለሚታወቁት የህወኃት ኮንትሮባንዲስቶች መስመሩን መክፈት ማለት ነው››የሚል ተቃውሞ እየተደመጠ ነው፡፡
ልብ ያለው ልብ ይበል--ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ አገራችን ለተዘፈቀችበት ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠትና ከገባችበት አዘቅት ለማውጣት ከህወኃት/ኢህአዴግ የምንጠብቀው ካለም ሙጣጭ ነው፡፡ ሁላችንም በመጨረሻው ሰዓት ላይ ነን፡፡ ‹‹ሟች ይዞን እንዳይሞት›› እና አገርን ለበለጠ ጥፋት እንዳይዳርግ የመከላከል- አገር-አድን ተግባርና ኃላፊነት የወደቀው በእኛ ፣በተለይና በበለጠ በትግራይ ልህቃን ጫንቃ ላይ ነው፡፡ ከዚህ መረዳት ያለብን--ከእንግዲህ ህወኃት ላለፉት 26 ዓመታት የዘራው የዘረኝነትና አድሎኣዊነት ፣የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲና አካባቢያዊና ዘር-ተኮር ግጭት ስልት በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ፍሬ ሊያፈራ ያለመቻሉን ብቻ ሳይሆን ዛሬም ህዝብ እምቢ ‹አንለያይም፣ አንከፋፈልም፣ አንጋጭም› ሲል የራሱን የክልልና ፌደራል ታጣቂ አሰማርቶ ግጭት እየቀሰቀሰና እያስፋፋ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም የፖለቲካ ድርጅቶችና አክቲቪስቶች ይህን ጠንቅቀን መረዳትና እንደሀዝቡ በኅብረት መቆም የነገ ሣይሆን የዛሬ ተግባር መሆኑን ነው፡፡
ስለሆነ እንደማመጥ፣ እንተባበር፣ እንከባበር---አቅማችንን አስተባብረን ትግላችንን አቀናጅተን ጊዜውን ለሚባጅ ፣ የተጋረጠብን አደጋ ለሚመጥን ዘላቂ መፍትሄ በኅብረት እንሥራ፡፡ ሁኔታው ከተለመደው ይለያል፣ በእጅጉ-- ያሳስባል፣ ያስፈራል ፡፡ ብንዘግይም ጨርሶ አልመሸብንም፡፡ ደግመን ደጋግመን በአካታች ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ--ለሽግግር ወቅት እንዘጋጅ --የሚለውን ጥሪ ዛሬም እናሰማለን፡፡ ዛሬ ‹‹ማን ከማን ተጣላ፤ አቋራጭ የሥልጣን ጥያቄ ነው›› የሚለው ምላሽ እንደማይሆን ፍንትው ብሎ በሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ ተረጋግጧል፡፡ ህወኃቶች ክህደት ወደመቃብር ያወርዳችኋልና…. ዕድሉን ተጠቀሙበት፤ መልዕክታችን ነው፡፡
ቸር-ቸሩን ያሳስበን ለአገርና ለህዝብ የሚበጀውን ያስተግብረን፡፡ በቸር ያገናኘን//

«
Next
Newer Post
»
Previous
Older Post

No comments:

Leave a Reply