Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

የኔስ ሔዋን ~ ክፍል - 2 [ከአስጌ]



የኔስ ሔዋን ~ ክፍል - 2 [ከአስጌ]

7ኛ ክፍል ግን አንድ አዲስ ነገር ተከሰተ። የ7ኛ ክፍል ትምህርት ከጀመርን 2ወራትን አሳልፈናል። በነዚህ የሁለት ወራት የትምህርት ጊዜ ውስጥ በጓደኛየ አማካኝነት አንዲት ሴት ልጅ ጋ ተዋውቄ ነበር።  

ልጅቱም በተከታታይ ወደኔ መመላለስዋንና በወሬ ማጥመድዋን ተያይዘዋለች። "ትሳፋርይዋ አድማጬ በጉጉት እየተከታተለች እሽ ከዛስ አለች።" ከዛማ አንድ ቀን በእረፍት ላይ ክላስ መጣችና የሆነ ነገር እንደሆነች መናገር ፈለገችና መልሳ የአማረኛ ደብተሬን ወስዳ በቤት አመጠዋለሁ ብላ ከተቀመጥንበት ተነስታ ወደ ክላስዋ ሄደች። 

እኔም የልጅቱ ሁኔታ ግራ ቢያጋባኝም ግን ምን እንደፈለገች መገመትና ማወቅ አልቻልኩም ነበር። ከእረፍት በውሀላ ያለውን ይ3ክፍለ ጊዜ ና የ2ሰአት ቆይታየ እጅግ ከባድ ነበር። እንዲያውም ምን ተከሰተ መሰለሽ እ ምን ተከሰት አለች በጉጉት የተፈጠረውን ለመስማት

ከእረፍት በውሀላ ያለውን ክፍለ ጊዜ መማር አቅቶኝ በጉጉት አንዴ መነሳት አንዴ መቀመጥ ብቻ ግን ምን እንደሆነች ስላላወኩ እጅግ ጓጉቼ ነበር። እናም በርበሩን መመልከቴን ተያያዝኩት። 

ከዛማ የ4ኛው ክፍለ ጊዜ ሲያልቅ መምህር ተከትየ ስወጣ መምህሩም ለምን ተከትለኸኝ ወጣህ በሚል ሰበብ ወደ ቢሮ ወሰደኝ። መምህሩና ዳይሬክተሩ አስተያየታቸው ሲያስፈራ ብታይ በስማም ገደል ይከታሉ።  

እኔም በመምህሩ ሁኔታ እየተገምኩ ዳይሬክተራችን ምን እንዳጠፋው ጠየቀ። መምህር ስንታየሁም ተቻኮለና እኔ እዛ ክላስ እምገባው እሱ ሲወጣ ነው ካለዛ አይሆንም እሽ እሱ ባለበት ክፍል አላስተምርም ብሎ ብሶቱን ተናገረ። 

እና ዳይሬክተሩ ምን አለህ ባክህ አለች የታሪኬ ተከታታይ ተሳፋሪዋ ጓደኛየ ዳይሬክተሩም እሽ መምህር ስንታየሁ ልጁን እኛ እናስተካክለዋለን እሽ አለና ወደኔ ተመለከተ። ከዛ እኔም ቀበል አደረኩና በፍጥነት አይ ጋሼ ይሄን ያክል ያስቼገርኩህ አልመሰለኝም ነበር።  

አልኩና እግሩ ስር ተደፍቼ ይቅርታ ጠየኩት። እና ይቅርታ አደረገልህ አለች ተሳፋርዋ ጓደኛየ። ከዛማ መምህሩና ዳይሬክተሩ እርስ በርስ ሲፈጠጡ በጨረፍታ ተመለከትኳቼው። መምህሩም በይሉኝታና በሼም ሳይፈልግ በግድ ይቅርታ አደረግልኝና ተለያየን። እኔም በሱ ፔሬድ በድጋሜ ላልረብሽና ላልፎርፍ ለራሴ ቃል ገባው። 

ይትምህርቱ ሰአት ሊያልቅ የቀረን 15 ደቂቃ ብቻ ነው። ይህችን 15 ደቂቃ እንዴት ላሳልፋት በጣም ሲበዛ እረዘመችብኝ። ማለት በቃ ሀሳቤ ሁሉ ልጅትዋ ጋር ሆነ ምን ሆና ይሄን፣ ምን አርጌያት ይሆን ፤ብቻ አላቅም በውስጤ ብዙ ሀሳቦችን እያመላለስኪ 15 ደቂቃው አልቆ ወደ ቤት እንድንሄድ የሚያበስረን ደወል ተደወለ እኔም ክፍል ገብቼ ፖርሳየን ይዤ ስወጣ ከርቀት ተመለከትኳት።  

ለመውጣት እየተዘጋጀው አስዋን መመልከቴን አላቆምኩም ነበር ግን ምንም አዲስ ነገር አላየሁም ያው ደብተሬን ይዛው መጣችና ከደብተሬ ውስጥ የሆነ ነገር ከትታ ሰጠችኝ። እኔም ምንድነው ብየ ጠየኩአት። 

መልሳ ቤት ብቻህን ሁነህ እየው አለችኝ። ተሳፋሪዋ ጓደኛየም እና ምንድነው የሰጠችህ አለች ለመስማት በመጓጓት። ያው ወደቤት እየተጣደፍኩ ሄድኩና ዶርሜ ገብቼ ፖርሳየን ከፈትኩና ያንን ደብተር አወጣውት.. .........

ክፍል 3 ይቀጥላል


የኔስ ሔዋን ~ ክፍል - 1 [ከአስጌ]

የኔስ ሔዋን ~ ክፍል - 1

ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ በመብረር ላይ ባለው የህዝብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ ገብተን (ተሳፍረን) መጓዝ ከጀመትን 1፡00 ይሆነናል።  


በጉዞው ውስጥ ሰወች የየራሳቸውን ምርጫ ተጠቅመው አንዳንዶቹ ስልካቼው ጋ ይታገላሉ። ሌሎች ደግሞ መፅሀፍትን ያያሉ። አንቻንዶች ደግሞ ተኝተዋል። 

ሰወችን ተዛውሬ ከተመለከትኩ በውሀላ እኔም የራሴን መደበርያ በመፈለግ ወደ ዋሌት ፖርሳየ እጀን በመላክ ከሆዋላ ኪሴችመዘዝ አድርጌ አውጥቼ ፎቶ ማየትና ማገላበጥ ስጀምር ከጎኔ የተቀመጠች አንድ እህቴ ( ተሳፋርይዋ ሴት ማለቴ ነው ) የማገላብጣቼውን ፎቶዎች ማየት እችል ይሆን በማለት በትህትና ጠየቀችኝ።

የልጅቱን ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር ተቀበልኩና ፎቶዎችን እያየው ወደስዋ አስተላልፈው ጀመር። ልጅቱ ሁሉንም ፎቶዎች አገለባብጣ ካየች በውሀላ ፎቶው ጋ በተደጋጋሚ አብሬያቼው ስለተነሰዋቼው ልጆች መጠየቅና ስለነሱ ማወቅ እንደምትፈልግ በፈገግታ ነገረችኝ።

እኔም የጓደኞቼን ፎቶ ተቀብየ በስነ ስርአት ለማስረዳትና ስለ ጓደኞቼ ታሪክ ለመናገር ና ለማስረዳት ያክል በትውስታ መስመር ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ከሚወስደን መኪና በሀሳብ ሰመመን ተመልሼ ባህር ዳር ገብቼ ስለነበርን የጓደኝነት ሁኔታ ማሰብና ማስታወስ ጀመርኩ። ትረካየንም በተረጋጋ መንፈስ የንዱን ጓደኛየን ፎቶ እየነካው መናገር ጀመርኩ።

ይሄ ጓደኛየ ብርሀኑ ይባላል እድሜው 17 ይሆነዋል። የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ይሄ ልጅ ሴት በጣም ነው እሚወደው። ግን ማናገር ስለሚፈራ ወድዋት ነው እሚቀረው እንጅ እስዋ ካልፈለገች እሱ አያናግራትም። ይሄኛው ደግሞ ዳንኤል ይባላል። 

10ኛ ክፍል ካጠናቀቀ 2አመት ሆኖታል። ሴት ናት የተባለች አታመልጠውም። መልክ ሀብት ምናምን አይልም ብቻ ግን ተቀምጣ ትሸናለች ከተባለ ለሱ ምርጫው ነች። ግን ሴቶች ሁሉ እንደሱ ስለሚመስሉት በጣም ነው የሚጠላቸውና የሚጠነቀቃቼው። ያለ ኮንዶም በፍፁም ሴክስ አያደርግቼውም።  

ይሄ ደግሞ መልካሙ ይባላል። የዩንቨርስቲ ተማሪ ነው በቀጣይ አመት ይመረቃል። መልካሙ በትምህርቱ በጣም ጎበዝ ነው። ግን አንዴ ወደየልጅነት 11ኛ ክፍል እንዳለፈ አቋርጦት ነበር። ምክንያቱም ፍቅር ነው። በጣም የሚያፈቅራትና የምታፈቅረው የነበረች ፍቅሩ አሜሪካ ልውሰድሽ ብሎ አታሎ በተዋት ሰውየ የከዳችውን ማስቴን ለመርሳት በሚል ምክምያት ነበር ያቋረጠው። 

መልኬ በትምህርቱየያዘው በጣም ጎበዝ ሰለነበር ቤተሰቦቹና አንዳንድ መካሪወቹ ጉትጎታ ማስቴን እረስቶ ወደ ትምህርቱ ተመልሶ አሁን ሊመረቅ አመትና ቀጣይ 1አመት ብቻ ነው የቀረው ግን መልኬ ከዛህን ጊዜ ወዲህ ሴት የተባለች እርሜ ብሎ ተቀመጠ።  

ሴት የተባለች ባጠገቡ ባታልፍ ደስታው ነው። አይደለም የሰውና የእንስሳም ቢሆን አትለፉብኝ የሚል ነው እሚመስለኝ።
ኦ !! ይቅርታ ስለኔ ሳልነግርሽ እኔ ያው እንደምታይኝ ለማያቁኝና ለሚጠሉኝ ነው እንጅ የማላምረው ለእናቴ ወርቅ ነኝ። እየቀለድኩ እንዳይመስለሽ ከምሬ ነው። ከወርቅም የበለጠ ወርቅ እንደሆንኩ ደጋግማ ስለምትነግረኝ ነው። 

እናትዬ እወድሻለሁ ግን ግን የማልዋሽሽ ነገር ቢኖር የመልኬ የድሮ ፍቅረኛው ጋ ተልኬ ስሄድ ምን ትለኝ ነበር መሰለሽ "አንተ የሆንክ አስፓልት ፊት" ምን አርጊ ነው እምትሉኝ። ስትለኝ እኔም ተልኬ ነው ብየ ንግግሬን ልጀምር ስጣደፍ ትቀጥልና 

ያንን መናጢ ደሀ ጓደኛህን ስትለው ድሀ ሲሰራና ሲማር እንጅ ሲያፈቅር አያምርበትም በለው ትልና አንተ ደግሞ እሱን ቅ/ሚካኤል የደበደበውን የሚመስለውን ፊትህን በዚህች መኪና ሳልገጭልህ እያለች መኪና እንደተገዛላት በጠቋሚ እጣትዋ ስታሳየኝ በንግግሯ ተናድጄ ወደ መጣውበት እበራለሁ።

አሁንም ይቅርታ ልጠይቅሽ ይቅርታ ፣አሽና አመሰግናለሁ እሚባሉት ቃላቶች ለሰው ልጅ አስፈላጊ ስለሆኑ ልንጠቀማቼው ይገባል። ስሜ ♥ናትናኤል ይባላል። እኔ ከጓደኞቼ አስበልጨ የምደወው እዮብን ነው። 

ምክናቱም ዳንኤል ሴትን ልጅ በመበቀል ስራ ተጠምዶ እንዲያቆም ስንጠይቀው መልካሙን ያሳመመችው ሴት ልጅ መልሳ አክማ እስክታድነው ድረስ ሴትን አልምርም እያለ ሴቶችን በማጭበርበር ና በመቅረብ ከሚያገኛት ሴት ጋ ሴክስ ያደርጋል። እኔም ይህንን ተግባሩን አልወድለትም። 

መልካሙ ደግሞ እፆታዋ ሴት የሆነች ሁሉ ተጎድታ ፣ታማ፣እቦዋት፣ወድቃ ተሰብራ፤ ወይም ወንድም ቢሆን እባክህንችእርዳኝ ብሎት ሚስቴ ልትሞትብኝ ነው ወይ እህቴ ወይ ፍቅረኛየ ካለው እንደቆመ ብትሞት ነው እሚመርጠው እንጅ አይረዳውም። ለሱ ሁሉም ሴቶች አንድ ናቼው። 

ብርሀኑም አንድ ችግር አለበት። የሴቶችን የማይቀርበው የተከዳውን መልኬን በማየትና በሚያተራምሰው ዳንኤልን ሲያይ ከዳኒ ጋ የሚተኙት ሴቶች ሁሉ እንደ ዳኒኤል ናቼው ብሎ ስለሚያስብ ነው። እናም እዮብም ከነሱ እማስበልጥበት ምክንያት ይሄው ነው። 

እዮባ አንድ ምርጥ አባባል አለችው። መልካም ሴት በትዕግስት እንጅ በፍለጋ አትገኝም ብሎ ስለሚያምን ነው። እኔ ግን አንደሱም አይደለሁም። እስከ 8 አመቴ ድረስ ገጠር ሲሆን ያደኩት ከዛ በ1988 ጥር17 ባህር ዳር ከተማ ገባን።

በዚህ ወቅት የኤች አይቪ በሽታ እየተስፋፋና እየተነገረለት የነበረበት ወቅት ሰለነበር አባቴ ሴት የምትባል ንገር ቀትቤ ካወራሁና አብሬያት ከተቀመጥኩ ኤች አይቪ ይዞኝ እንደምሞትና ከቤትም እንደሚያባርረኝ በሰፊው ይሰብከኝ ሰለነበር ቃሉን ስላጓድል እስከ 7ኛ ክፍል ድረስ በፍቅርና በደስታ ቤተሰቤ ጋ እያሳለፍኩ ባለውበት ላይ 7ኛ ክፍል እንደገባው አንድ አዲስ ነገር ተከሰተ.. ........

ክፍል 2 ይቀጥላል

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ - [ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው]

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በዚህ መልክ አብን ቢሮ ይገኛሉ። ወጣቶቹ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ፍትህ እናገኛለን ብለው ነበር።  


ሆኖም የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የአብንን ቢሮ ከብቦ ወጥተው አቤቱታቸውን እንዳያሰሙ አግዷቸዋል። "ከወጡ እንተኩሳለን" እያለ መዛቱ ተገልፆአል።

ለወጣቶቹ ተራ ጀሮ ጠቢና ፖሊስ መላኩ አይደለም የሚገርመው። አንድ ከሰራዊቱ የወጣና በየጋዜጣው "ሪፎርም ያስፈልጋል" ሲል የምናውቀው ጀኔራልም ሁኔታውን ለማየት በቢሮው በኩል ሲያልፍ ተመልከቻለሁ። እንግዲህ የትህነግን ሰላዮች ስምሪት የሚቆጣጠረውና ወደ መቀሌ ሪፖርት የሚያጠናቅረው ይህ ጀኔራል ይሆናል።
ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ
ወልቃይት ጠገዴ 1983 ዓ.ም በትግራይ መንግስት በኃይል መያዙ ይታወሳል፡፡ የትግራይ መንግስት ወልቃይት ጠገዴ የማንንት ጥያቄ ባቀረቡ የወልቃይት አማራዎች ላይ አስር፤ሰቆቃ፣ ግድያ ሲፈፀም ቆይቷል፡፡

የትግራይ መንግስት አማራዎችን በማፈናቀል በአንፃሩ የህዝቡን ስብጠር ለመቀየር ትግሬዎችን ከአድዋ፣ ከአድግራት፣ ከአንደርታ፣ ከአክሱም… ወዘተ በማምጣት በወልቃይት ለም መሬቶች ላይ አስፍሯል፡፡

በአካባቢው የትግራይ መንግስት በዘረጋው የአፈና መዋቅር የወልቃይት ጠገዴ አማራ ተወላጅ ላይ የተጠና አስተዳደራዊ በደል እየፈፀመ ይገኛል፡፡ ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴርም እየተፈፀመ ያለውን በደል እንዲረዳና አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን የሚከተሉትን ዋና ዋና ጥያቀዎቻችን እናቀርባለን፡፡

  • የትግራይ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ አማራ ላይ የሚፈፅመውን ግድያ፣ አፈና፣ሰቆቃ፣አስር እና መፈናቀል በአስቸኳይ እንዲያቆም 
  • የወልቃይት ጠገዴ አማራዋች በቋንቋችን በአማርኛ የመናገር የመማር የመፃፍ፤በበህላችን ሀዘንና ደስታችን የመግለፅ መብታችን አንዲከበር
  • በትግራይ መንግስት የሚፈፀም የመሬት ዝርፊያ እንዲቆምልን እና ሐብት ንብረት የማፍራት መብታችን እንዲረጋገጥ
  • በማንነታቸው ምክንያት ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው ሶሮቃ ጎንደር አዲስ አበባ በጊዚያዊ መጠለያ የሚገኝ የወልቃይት ጠገዴ አማራዎች በአስቸኳይ ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱና የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ እንዲደረግ

  • ትግራይ ፀጥታ አካላት ወልቃይት ጠገዴን ለቀው እንዲወጡ እና የፌደርል የፀጥታ አካላት በቦታው እንዲተኩ እንዲደረግ
  • የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማነንነት ጥያቄ በአስቸኳይ እንዲመለስ 
  • ወደ ወልቃይት ጠገዴ የመጡ የትግራይ ሰፋሪዎች በማንነታችን ጥያቄ ላይ የሚፈፅሙትን ሴራና ደባ እንዲቆሙልን
ለወጣቶቹ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ አራት ኪሎ ግንፍሌ ከድልድዩ ወደ ጃንሜዳ በሚወስደው መንገድ በኩል የሚገኘው የአብን ቢሮ በመሄድ ማገዝ ትችላላችሁ።
ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በአዲስ አበባ

የእውነተኛው የአፍሪካ አባት ሐውልት በጥር ወር ይጠናቀቃል! (አቻምየለህ ታምሩ)

የእውነተኛው የአፍሪካ አባት ሐውልት በጥር ወር ይጠናቀቃል! (አቻምየለህ ታምሩ)

በወያኔ የአፓርታይድ አገዛዝ ተቃውሞ ቢቀርብበትም በጋና መንግሥት ብርታትና ግፊት የሌሎችን የአፍሪካ አገሮች ይሁንታ በማግኘቱ በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ግንባታው የተጀመረው የእውነተኛው አፍሪካ አባት የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት በመጪው ጥር ወር እንደሚመረቅ ኅብረቱ አስታውቋል።

መለስ ዜናዊ ክዋሜ ንክሩማህን የአፍሪካ አባት ያደረገው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ያዋረደ መስሎት ነበር። ሆኖም ግን እውነት ይዘገያል እንጂ ተደብቆ አይቀርምና በእውነተኛ የአፍሪካ ልጆች ተጋድሎ የእውነተኛው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባት መታሰቢያ ሐውልት ለምርቃት ሊበቃ ነው። 


የሚጣላ ሕሊና ያላቸው ሰዎች እስካሉ ድረስ ለእውነት የደከሙ ደዎች ስም፣ ታሪክና ስራ አንድ ቀን ከመቃብር በላይ መዋሉ አይቀርም!

ከታት የታተመው ድምጽ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመጀመሪያው የክብር ፕሬዝደንት የሆኑት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረት ግንቦት 14 ቀን 1955 ዓ.ም. ያሰሙት ታሪካዊ ንግግር ነው።

በግርማዊ ጃንሆይና ረዳቶቻቸው የረቀቀ ዲፕሎማሲ ጥረት ወደ አዲስ አበባ ለጉባዔ የተጋበዙት ነፃ የወጡ የአፍሪካ መሪዎች ኢትዮጵያ ያዘጋጀችውን የኅብረቱን ቻርተር የፈረሙት በዚህ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታሪካዊ ንግግር በቀረበላቸው ጥሪ መሰረት ነበር።

መረጃ በአሰቦት ገዳም ጉዳይ - ሃብታሙ አያሌው



መረጃ በአሰቦት ገዳም ጉዳይ - ሃብታሙ አያሌው

ከአንድ ሳምንት በፊት አመሻሽ ላይ ወደ ገዳሙ የመጡት ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች መነኮሳቱ ገዳሙን ለቀው እንዲሄዱ በማስፈራራታቸው ደውል ተደውሎ ምዕመናን ሲሰባሰቡ ታጣቂዎቹ ሸሽተው ወደ ጫካው መግባታቸው እና በቀጣዩም ቀን ወደ መነኮሳቱ መኖሪያ ድንጋይ ሲወረወር ማምሸቱም ተነገረ።

የገዳሙ መነኮሳት ለወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ስጋታቸውን በፅሑፍ አስገቡ። ያንን ተከትሎ ወረዳው የመደባቸው ታጣቂ ሚኒሻዎች በቦታው ሲደርሱ ከገዳሙ ጠባቂዎች ጋለ አለመግባባት ተከሰተ። 


የወረዳው ፖሊስ ከአንድ ጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ መነኮሳቱ ስጋታቸውን እና የተፈጠረውን ሁኔታው በፅሑፍ ማቅረባቸውን አምኖ፤ ፖሊስ ድጋፍ ለመስጠት ከላካቸው ሚኒሻዎች ጋር የተፈጠረው አለመግባባት ግን ባለመተዋወቅ የተከሰተ እንደሆነ መፍትሄ እንደተሰጠው ተናግሯል። 

አያይዞም አሁን የገዳሙ ጠባቂዎች እና በወረዳው የተመደቡ ሚሊሻዎች በጋራ እየጠበቁ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ለአንድ ሳምንት የዘለቀው አስጨናቂ የገዳሙ ሁኔታ በቤተክርስቲያን ጉዳይ ታዋቂ የሆነው "ሐራ ተዋህዶ" ዌብሳይትን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎች ሲዘግቡት ቆይተዋል። 

በተለይም ገዳሙ የሚገኘው የተደራጁ ኃይሎች የሐረርን ህዝብ በውሃ ጥም እየቀጡ እንዲሁም በጥቅሉ ከድሬዳዋ እስከ ሐረር መኪና እያስቆሙ እየዘረፉ ባለበት አካባቢ መሆኑ። ይህ ሁኔታም በመንግስት ሚዲያዎች እና በአካባቢው ጉዳተኞች እየተነገረ በመሆኑ ሁኔታው በእጅጉ ብዙዎችን አስጨንቋል።

ባለሁበት አገር ለሊቱ በመንጋት ላይ እስከሚገኝበት ሰዓት የገዳሙን ሁኔታ በመከታተል ያገኘሁት መረጃ ከላይ የተመለከተውን ነው። አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የገዳሙ ነዋሪ የሚዲያውን ተፅዕኖ ተከትሎ መነኮሳቱ ምንም አልተፈጠረም እንዲሉ እና ስጋቱን አሳንሰው እንዲናገሩ እንደታዘዙ ሚዲያም ለዚሁ ጉዳይ ወደ ቦታው እንደሚላክ ጠቁመዋል።

ዋናው እና ተፈላጊው ነገር የፖለቲካ እሰጥ አገባው ሳይሆን የታሪክ አሻራ የሆነው ገዳም እና መነኮሳቱ ደህና መሆናቸው ነው። በቅርቡ በሶማሌ ክልል በርካታ አብያተ ክርስቲያናት የወደሙት እና መነኮሳት በቁም በእሳት አርረው እንዲከስሉ የተደረጉት ከሶስት ወራት በፊት የደረሰባቸውን ዛቻ ሲናገሩ ሰሚ በማጣታቸው እንደሆነ የተገለፀው ከጉዳቱ መድረስ በኋላ ነው።

የወረዳው ፖሊስ ሚሊሻ መመደቡን መግለፁ የሚያስመሰግን ነው። የክልሉ መንግስት ግን በየቦታው ሚሊሻ መድቦ እሳት በነደደበት ሁሉ እሩጦ መፍትሄ ለመስጠት መሞከር ብዙ እርቀት አይወስደውምና አሁንም በህግ የበላይነት መከበር በኩል የዜጎች ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ ሊያደርግ ይገባል።

ችግር እያድበሰበሱ እያቃለሉ እየሸፋፈኑ ማለፍ አይበጅምን የፖለቲካ ድራማው ቀርቶ እውነተኛ መፍትሄ ይሰጥ። ነገሩን መካድ ችግሩን አይፈታውም። 27 ዓመታት በዚህ መንገድ ኑረናል። እናትን በጥይት የደፉት ልጇን ታሞ ነው የሞተው ሲያሰኙ ሰምተናል።  

ደህንነት ቢሮ ሲደበድቡት የሞተው የሐረሩን ኑረዲንን አስከሬኑን በገመድ አንጠልጥለው ተፀፅቶ ሞተ ብለው በኢቲቪ አሳይተው ደም አስነብተውናል። እውነት የወጣው ዘግይቶ ነው እናም የአሰቦት ገዳምን ጉዳይ እንደ እንደዛ ለማድረግ ባትሞክሩ ጥሩ ይመስለኛል።
ቢያንስ ገዳሙ በጋራ እየተጠበቀ መሆኑ እፎይታ ነው። ምንም ያልተፈጠረ ለማስመሰል መሞከረ መተማመንን
የባሰ ገደል ይከታልና ተወት አድርጉት።


"ማንነትን የመለሰ ፌዴራሊዝም ስህተቱን የሚያርምበት አቀበት ላይ መላ ሊያጣ አይገባም" - ጥናት



"ማንነትን የመለሰ ፌዴራሊዝም ስህተቱን የሚያርምበት አቀበት ላይ መላ ሊያጣ አይገባም" - ጥናት

  • ‹‹ሕገ መንግሥቱ የወልቃይት እና የራያን ጥያቄ መመለስ ያልቻለው ሕዝቦቹ በየት እንደሚተዳደሩ ቅድሚያ ስላልተጠየቁ ነው፡፡››
  • ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ሕገ-መንግሥት ተጻፈ እንጂ አልተተገበረም፡፡›› የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር
  • ‹‹አሁን የወልቃይት ጥያቄ የማንነት እና የመሬት ይገባኛል ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲ እና ችግሩን የሚፈታ ሕገ መንግሥት ጭምር ነው›› ዶክተር ሶኛ ጆን
  • ‹‹ማንነትን የመለሰ ፌዴራሊዝም ስህተቱን የሚያርምበት አቀበት ላይ መላ ሊያጣ አይገባም፡፡›› ጥናት
ባሕር ዳር፡ጥቅምት 16/2011 ዓ.ም(አብመድ) የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህሩ ቻላቸው ታረቀኝ ‹‹ሕገ መንግሥቱ የወልቃይት እና የራያን ጥያቄ መመለስ ያልቻለው ሕዝቦቹ በየት እንደሚተዳደሩ ቅድሚያ ስላልተጠየቁ ነው፡፡ አንቀፅ 46 የግዛት ወሰን ላይ ቋንቋ፣ አሰፋፈር እና የሰዎች ይሁንታ ይላል፡፡

ነገር ግን በ1984 ክልሎች ‹አንድ፣ ሁለት …› ተብለው ሲለዩ የተካለሉበት በ1987 ሕገ-መንግሥቱ ሲፀድቅ ያለ ሕዝብ ይሁንታ በዚያው ቀጥሏል›› ብለዋል፡፡ ይህም አሁን ላሉት ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄዎች በር መክፈቱንም ጠቁመዋል፡፡


መምህር ቻላቸው ‹‹የሕዝቦች ፍላጎት ቀሰበቀስ ሲቀሰቀስ በዛ ልክ የተሰፈረው ሕገ-መንግሥት መመለስ የሚችልበት አቋም ላይ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሕገ-መንግሥት ተጻፈ እንጂ አልተተገበረም፤ የፖለቲካ ወገንተኝነት እና ጥገኛ ተቋማት እንደአሸን ነበሩ፡፡  

አሁንም ችግሩን ለመፍታት በሕገ-መንግሥቱ ታሪካዊ ማንነት ሊካተት ይገባል›› በማለት መፍትሔ ያሉትን ሐሳብም ምሁሩ ሰንዝረዋል፡፡ የግዛት ወሰን ችግሮች ሲኖሩም መፍትሔውን ጥያቄ ለሚነሳበት ክልል መንግሥት ከመስጠት ይልቅ የፌዴራል መንግሥት የሚወስንበት አሠራር ቢኖር እንደሚሻልም ተናግረዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካል ሳይንስ እና የዓለምዓቀፍ ጥናት ትምህርት ክፍል ተመራማሪው ዶክተር ሶኛ ጆን ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት እና የወልቃይት ጥያቄ ሆድና ጀርባ ናቸው›› የሚል ሐሳብ አንስተዋል፡፡ ‹‹የዜጎች ጥያቄ እና የሕገ መንግሥቱ ዝምታ ከጊዜ ወደጊዜ አሳሳቢ ነው፡፡  

የወልቃይት ነዋሪዎች አንቀፅ 39 ባለው መብት እና አንቀፅ 46 ባስቀመጠው መሠረት ‹ቋንቋችን፣ ማንነታችን እና ባሕላችን አማራ ሁኖ ሳለ በሌላ ክልል እንተዳደራለን› የሚል ቅሬታ አላቸው፡፡ ሕገ-መንግሥቱ በቀጥታ እኛን ያላማከለ ውሳኔ በማሳለፉ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እና እስር እየተዳረግን ነው›› ማለታቸውን ጥናታቸውን ዋቢ አድርገው ዶክተር ጆን ገልጸዋል፡፡ 

‹‹አሁን የወልቃይት ጥያቄ ‹የማንነት እና የመሬት ይገባኛል› ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲ እና ችግሩን የሚፈታ ሕገ-መንግሥት ጭምር ነው›› ብለዋል ዶክተር ሶኛ ጆን፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ጥናት አቅራቢ መምህር ቢንያም መኮንን ደግሞ ‹‹በብሔር ላይ የተመሠረተው ፌዴራሊዝም የሕዝቡን ምጣኔ ሀብታዊ ፍላጎት የመመለስ ፈተና ላይ ወድቋል፡፡  

ማንነትን የመለሰ ፌዴራሊዝም ስህተቱን የሚያርምበት አቀበት ላይ መላ ሊያጣ አይገባም፡፡ የግለሰብ ነፃነት ላይ የተመሠረተ፣ ምጣኔ ሀብታዊ ተጠቃሚነትን ሊያሻሽል የሚችል ሥርዓት መፍጠር መፍትሔ ነው፡፡ ከማንነት ባሻገር ደግሞ የጋራ እሴቶችና ጥቅሞች ላይ መረባረብ ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡

ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን የጥናትና ምርምር ዓውደ ጥናት በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ዘጠኝ ምርምሮች ቀርበውበት ተጠናቋል፡፡

ዘጋቢ፡-ግርማ ተጫነ


የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ስልጣን ለቀቁ



የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ስልጣን ለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 16/2011) የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ስልጣናቸውን ለቀቁ። አዲስ ፕሬዝዳንትም ተሰይሟል።

በአዲስ አበባ ለአንድ ሳምንት ግምገማ ሲያደርግ የቆየው የጋምቤላ ክልል ገዢ ፓርቲ በገዛ ፈቃዳቸው የለቀቁትን ሊቀመንበሩንና ምክትላቸውን በሌሎች መተካቱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበርና የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ጋትሉዋክ ቱትና ምክትላቸው አቶ ሰናይ አኩዎር ይቅርታ ጠይቀው በለቀቁበት የአዲስ አበባው ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መገኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በጋምቤላ የጋትሉዋክ ቱት አመራር ከስልጣን እንዲወርድ የተቃውሞ ሰልፍ ሲደረግ ቆይቷል። በዚህ ተቃውሞ በተወሰደ የሃይል ርምጃም በትንሹ አስር ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። ለወራት የዘለቀው የህዝብ ጩሀት በመጨረሻም ሰሚ አገኘ።

የጋምቤላ ክልል ነዋሪ አመራሩ እንዲነሳለት ህይወቱን የገበረለትን ተቃውሞ ሲያደርግ ነበር የቆየው። ባለፉት ሶስት ወራት በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ለፌደራሉ መንግስት ጥያቄ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።

በአመራር ላይ ያለው የጋትሉዋክ አስተዳደር በኢትዮጵያ የመጠውን የለውጥ ሂደት የሚያደናቅፍ ከመሆኑ ባሻገር የህወሀት የጭቆና አገዛዝን ማስቀጠል የመረጠ በመሆኑ በአስቸኳይ ይነሳ የሚለው ጥያቄ ተነስቷል።

ተቃውሞው በተለይ የክልሉ ፕሬዝዳንት ላይ ያነጣጠረ ነበር።

ለዚህም ሁለት ምክንያቶች ይነሳሉ። አንደኛው የክልሉ ፕሬዝዳንት ጋትሉዋክ ቱት በትውልድ ደቡብ ሱዳናዊ በመሆናቸው በስደት ወደኢትዮጵያ ለገቡትና በቁጥር በጋምቤላ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ለሚበልጡ ደቡብ ሱዳናውያን ያደላሉ የሚል ነው።

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከህወሀት አገዛዝ ጋር እጅና ጓንት ሆነው የክልሉን ህዝብ ለጭቆናና ብዝበዛ እየዳረጉት እንደሆነ ይጠቀሳል።

የህወሃት ዘመን አፈናና በደል ጋምቤላ ተጠናክሮ መቀጠሉን ህዝቡ በምሬት ይገልጻል።

በቅርቡ ለውጡን ለመታዘብ ሀገር ቤት የገቡትን በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆኑት ዶክተር ማኛንግን ጨምሮ ከ10 በላይ አክቲቪስቶችን የግትሉዋክ ቱት አስተዳደር ማሰሩ ተቃውሞውን አጠናክሮታል።

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ፕሬዝዳንት አቶ ኦባንግ ሜቶ ወደ ጋምቤላ ባመሩ ጊዜ የጋቱዋክ ቱት አመራር የፈጠረውን ችግር መነሻ በማድረግ በአዲስ አበባ መግለጫ የሰጡት አቶ ኦባንግ የፌደራሉ መንግስት በጋምቤላ አስተዳደር ላይ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቃቸውም የሚታወስ ነው።

ለወራት የህዝብ ብሶትና እሮሮ ከተሰማ በኋላ ትላንት ምላሽ መገኘቱን ነው የደረሰን መረጃ የሚያመለክተው።

አዲስ አበባ የገቡትና ግምገማቸውን ከጀመሩ አንድ ሳምንት የሆናቸው የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጋህአዴን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከአንድ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን አሳውቀዋል።

ህዝብ ለውጥ እንደሚፈልግ፣ አመራሩ እንቅፋት ሆኖ እንደቆየ አባላቱ ጠንከር ያለ ግምገማ ማድረጋቸውን ተከትሎ የህዝብ ተቃውሞ የቀረበባቸው አቶ ጋትሉዋክ ቱትና ምክትላቸው አቶ ሰናይ አኩዎር በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ተስምቷል።

ፓርቲው አቶ ኦሙድ ኡጁሉን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አኙአያ ጃከን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡም ታውቋል፡፡ አቶ ኦሙድ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ክልሉን እንደሚመሩ ነው የተገለጸው።

በግምገማው ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ መገኘታቸው ታውቋል።

የክልሉ ህዝብ ልማት የተጠማ በመሆኑ አዲሱ አመራር ጊዜውን በግል አጀንዳዎችና ሽኩቻ ከማጥፋ ይልቅ ራሱን ከጎሰኝነትና ከጥላቻ በማጽዳት የክልሉን አመራር በማጠናከር የህዝቡን ችግር ሊፈታ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ገልጸዋል።

ከኃላፊነት የተነሱት አመራሮችም በድርጊታቸው ተጸጽተው ይቅርታ መጠየቃቸው እና ህዝቡን ለመካስ በተመደቡበት የስራ መስክ ለመሰማራት መወሰናቸውም ተመክልቷል።

ኢሳት ያነጋገራቸው የጋምቤላ አክቲቪስቶች ግን የጋትሉዋክ አመራር አባላት ለፈጸሙት የግድያና የዘረፋ ወንጀል በህግ ሊጠይቁ ይገባል ባይ ናቸው።