- ‹‹ሕገ መንግሥቱ የወልቃይት እና የራያን ጥያቄ መመለስ ያልቻለው ሕዝቦቹ በየት እንደሚተዳደሩ ቅድሚያ ስላልተጠየቁ ነው፡፡››
- ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ሕገ-መንግሥት ተጻፈ እንጂ አልተተገበረም፡፡›› የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር
- ‹‹አሁን የወልቃይት ጥያቄ የማንነት እና የመሬት ይገባኛል ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲ እና ችግሩን የሚፈታ ሕገ መንግሥት ጭምር ነው›› ዶክተር ሶኛ ጆን
- ‹‹ማንነትን የመለሰ ፌዴራሊዝም ስህተቱን የሚያርምበት አቀበት ላይ መላ ሊያጣ አይገባም፡፡›› ጥናት
ነገር ግን በ1984 ክልሎች ‹አንድ፣ ሁለት …› ተብለው ሲለዩ የተካለሉበት በ1987 ሕገ-መንግሥቱ ሲፀድቅ ያለ ሕዝብ ይሁንታ በዚያው ቀጥሏል›› ብለዋል፡፡ ይህም አሁን ላሉት ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄዎች በር መክፈቱንም ጠቁመዋል፡፡
መምህር ቻላቸው ‹‹የሕዝቦች ፍላጎት ቀሰበቀስ ሲቀሰቀስ በዛ ልክ የተሰፈረው ሕገ-መንግሥት መመለስ የሚችልበት አቋም ላይ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሕገ-መንግሥት ተጻፈ እንጂ አልተተገበረም፤ የፖለቲካ ወገንተኝነት እና ጥገኛ ተቋማት እንደአሸን ነበሩ፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካል ሳይንስ እና የዓለምዓቀፍ ጥናት ትምህርት ክፍል ተመራማሪው ዶክተር ሶኛ ጆን ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት እና የወልቃይት ጥያቄ ሆድና ጀርባ ናቸው›› የሚል ሐሳብ አንስተዋል፡፡ ‹‹የዜጎች ጥያቄ እና የሕገ መንግሥቱ ዝምታ ከጊዜ ወደጊዜ አሳሳቢ ነው፡፡
‹‹አሁን የወልቃይት ጥያቄ ‹የማንነት እና የመሬት ይገባኛል› ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲ እና ችግሩን የሚፈታ ሕገ-መንግሥት ጭምር ነው›› ብለዋል ዶክተር ሶኛ ጆን፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ጥናት አቅራቢ መምህር ቢንያም መኮንን ደግሞ ‹‹በብሔር ላይ የተመሠረተው ፌዴራሊዝም የሕዝቡን ምጣኔ ሀብታዊ ፍላጎት የመመለስ ፈተና ላይ ወድቋል፡፡
ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን የጥናትና ምርምር ዓውደ ጥናት በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ዘጠኝ ምርምሮች ቀርበውበት ተጠናቋል፡፡
ዘጋቢ፡-ግርማ ተጫነ
No comments: