የቀድሞ የፓርላማ አባልና የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት የነበሩት የአቶ
ግርማ ሰይፉ “የተከበሩት” እና በአረና እና በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ባለው የፖለቲካ ተሳትፎ የሚታወቀው አስራት አብርሀም ‹‹የህገ-መንግስቱ ፈረሰኞች›› የተሰኙት መፅሀፍት ለንባብ በቅቷል።
መፅሃፎቹ ከያዙት ቁምነገሮች ውስጥ ጥቂቶቹን እነሆ
ከግርማ ሰይፉ "የተከበሩት"ን ላስቀድም
"የኢህአዴግ መንግሥት እያደረገ ያለው ተግባር በህወሓት ጊዜ እንደነበረው ወደ ትጥቅ ትግል ሳይሆን ወደ መደበኛ ያልሆነ ነገር ግን ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ በበቀል ስሜት የሚደራጅ "አሸባሪነት" ሊስፋፋ የሚችልበት እድል እጅ እና እግር አውጥቶ ይታየኛል። ይህ ጨለምተኝነትን አይደለም ብሶት ሊወልደው የሚችል፤ በሰላማዊ ትግል ለውጥ ሊመጣ አይችልም በሚል ተስፋ ሲጨልም ግልፅ ብሎ እንደ ብርሃን የሚታይ ሃቅ ነው"
"ሬዲዮ ፋና በ1987 ተመሰረትኩ ይበል እንጂ ከጫካ ጀምሮ የኢህአዴግ ልሳን ሆኖ የመጣ የሚዲያ ተቋም ነው። በኢትዮጵያ ህግ ፓርቲዎች የሬዲዮ ጣቢያ ለማቋቋም ቢከለከሉም ገዢው ፓርቲ በግል ተቋም ስም በማቋቋም በፈለገው ጊዜ ካርድ እየመዘዘ አጀንዳ ማስቀመጫ እና ህዝብን ማወናበጃ አድርጎታል"
"ሃብታሙ አያሌው ለሰላማዊ ትግል ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ቢሆንም ሁለት ዓመት በእስር ከመንገላታት እና ለከፍተኛ ህመም ከመጋለጥ ሊታደገው አልቻለም። ከዘግናኝ የማዕከላዊ ምርመራ ምንም ውጤት ሳይገኝ ቢቀርም ለዚህ ልጅ ጥቃት ካሳ፣ ለሌሎችም የወደፊት ከለላ የሚሆን ነገር ከምክር ቤቱም ሆነ ከሌላ አካል ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም"ወደ አስራት አብርሃም "የሕገ መንግስቱ ፈረሰኞች" መፅሐፍ ሳልፍ
"ሕገ መንግሥት የአንድ ድርጅት ፕሮግራም ማለት አይደለም። አንድ ሃገር በጠቅላላ የሚተዳደርበት ቀዳሚ ሕጎችን የያዘ ሰነድ ማለት ነው። እንደዚህ ከሆነ ደግሞ የሁሉም ህዝብ እንኳ ባይሆን ቢያንስ የአብዛኛው ህዝብ እምነት የሚንፀባረቅበት ሕገ መንግሥት ነው መሆን ያለበት። አሁን እያየነው ያለው ሕገ መንግሥት ግን በዋናነት ህወሓትና ኦነግ ሆነው አስቀድመው በሽግግሩ ቻርተር ያፀደቁትን ነው ትንሽ ነገር ተጨማምሮበት ሕገ መንግሥት የሆነው። በመሆኑም ይህ የድርጅቱን እንጂ የህዝቡን ፍላጎት ያቀፈ አይደለም"
ከሱማሌ ክልል የመጡ ጉባኤተኛ የተናገሩት በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ የመግለጽ ሃይል አለው። ተረቱ እንዲህ ነው፣ "በሱማሌ ብሄረሰብ ኡጋል ቪዳር የተባሉ ታዋቂ ሰው ከእለታት በአንዱ ቀን ሸረሪት በአፍንጫቸው ላይ በማረፏ 'ኡ…ኡ…' ብለው ይጮኻሉ። በዚህ ምክንያት የመንደሩ ሰው ተሰብስቦ 'ምን ሆኑ?' ቢላቸው 'አፍንጫዬ ላይ ሸረሪት አረፈችብኝ' ይላሉ። 'ታዲያ ሸረሪት እኮ የምታስፈራ፤ ይህን ያህልም የምታስጮህ ነገር አይደለችም' ቢላቸው 'እኔ የጮህኩት ሸረሪቷን ፈርቼ አይደለም፤ ይህ አፍንጫዬ የአራዊት መፈንጫ መሆኑ አሳዝኖኝ እንጂ' አሉ ይባላል"እያለ ይቀጥላል። መፅሐፍቶቹን ማንበብ የወያኔን ምንነትና ማንነት፤ ሃገራችንን ወዴት እየመሯት እንደሆነ በግልፅ መረዳት ነውና ያንብቡት። መፅሐፎቹን በአሜሪካ
የኢትዮጵያ ሁኔታም እንደዚያ ነው የሆነው። መሪዎቿ በነበራቸው የስልጣን ጥማትና ራስ ወዳድነት ምክንያት ነገሮች በሰዓት ማረምና ማስተካከል አልተቻለም ነበር፤ በዚህም ምክንያት በመጨረሻ እንዲህ ባለ እጣ ፈንታ ላይ ጥሏታል
ቨርጂኒያ ስካይ ላይን
ዳማ ሬስቶራንት
አዋሽ ማርኬት
ናዝሬት ማርኬት
ውቤ በረሃ ማርኬት
መዐዛ ሬስቶራንት
ህብር ሬስቶራንት
ሜሪላንድ
ናዝሬት ስቶር
ኒውሀምሸር ላይ የሚገኘው ሸገር ማርኬት
አዲሱ ገበያ የገበያ ማዕከል
ጀራንየም ማርኬት
ዋሽንግተን ዲሲ
ጨርጨር ሬስቶራንት
እንዲሁም በኢንተርኔት መግዛት ለምትሹ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መግዛት ትችላላችሁ።
https://meshcart.com/products/by-girma-seifu
መልካም ንባብ።
No comments: