headlines

    3:35 PM
Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

» » » በሀገሪቱ እየሰፈነ ያለው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ባንዲራንም ስለሚያጠቃልል የሌላኛውን አስተሳሰብ መግፋት አይገባም- ጠ/ር ዶ/ር አብይ
First Ethiopianism

 የሌላኛውን አስተሳሰብ መግፋት አይገባም

(ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀገሪቱ እየሰፈነ ያለው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ባንዲራንም ስለሚያጠቃልል የሌላኛውን አስተሳሰብ መግፋት አይገባም አሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፥ በሀገሪቱ የመጣው ለውጥ ብቸኛ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ ስለሆነ ከውጭ የሚገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች የማግለል አካሄድን ሊከተሉ አይገባም ሲሉ ተናግረዋል።

በተናጥል በመፎከር አሸናፊ መሆን ስለማይቻል ተነጋግሮ በመግባባት መተባበር ይገባል ሲሉም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ።

ተፎካካሪ ፖለቲከኞች በሰጥቶ መቀበልና በመተባበር በኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሀገሪቱ እየሰፈነ ያለው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ባንዲራንም የሚያጠቃልል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ ሰንደቅ አላማን ምክንያት በማድረግ ሀገርን ለማበጣበጥ መሞከር ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ መከንያት ለውድመት፣ ለግጭት እንዳይዳረግም አሳስበዋል።

በረባ ባልረባ ጉዳይ ጉልበቱን ለማሳየት የሚጥር ሀየል ካለ እንጋደላለን እንጂ አሸናፊ መሆን እንደማይቻልም አስታውቀዋል።

ባንዲራ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ከሆነ ተመካከሮበትና ድምጽ ሰጥቶ መቀየር ይቻላል ሲሉም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበይ።

ካልሆነ ግን በጉልበት እኔ ባልኩት ብቻ ይሁን የምንል ከሆነ ኢትዮጵያን ማፍረስ ይሆናል ሲሉም አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አክለውም፥ ከውጭ የሚገቡ ሀይሎችን አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ ሄደን የምቀበለው እኛ አሸናፊ እነሱም አሸናፊ በመሆናቸው ነው ሲሉም ተናግረዋል።

«
Next
Ethiopia capital rocked by flag crisis; PM, police chief warn saboteurs
»
Previous
Ethiopia’s new leader is whittling away the old guard’s power
Pages 22123456 »

No comments:

Leave a Reply