Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

» » » ኢትዮጵያን ወደ ገደል እየከተተ ያለው የእርኩስ አገዛዝ እርኩስ ህገ-መንግስት (ሚኒሊክ ሳልሳዊ)


ኢትዮጵያን እየመራሁ ነው የሚለው አገዛዝ ከሽፏል፤ አስቸኳይ መፍትሔ ካልተፈለገ ኢትዮጵያ መንግስት አልባ ትሆናለች ፤ ኢሕአዴግ ራሱ ባወጣቸው ሕጎች ራሱን ጠልፎ ጥሏል። ዜጎች በገዛ ሃገራቸው በገዛ ወገኖቻቸው ሲፈናቀሉ ማየት ያማል። ይህ የወያኔ የመከፋፈልና ቂም የማያያዝ የማፋጀት አንዱ ፖሊሲው ነው። ይህ ደግሞ ዜጎች በገዛ ሃገራቸው እንዳይኖሩ እንዳይሰሩ ያደረገ ሲሆን ዜጎች በፍርሃት እንዲናጡ አድርጓል። ዜጎች በገዛ ሃገራቸው ተዘዋውረው የመስራትና የመኖር መብታቸውን በተመለከተ በተደጋጋሚ ጮኸናል ። እየጮህንም ነው። ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን የምትሆነው ዜጎች በየክልሉ ሰርተው መኖር ሲችሉ ነው።

ስራ ለመቀጠር ብሄርና የኣከባቢ መታወቂያ ጎጥና የቅርብ ዝምድና ጥያቄ ሊወገድ ይገባል። በሕዝቦች እኩልነት ላይ የተመሰረተ ሕገ መንግስትን መፍጠር የሚችሉች ሕዝቦች እንጂ የከሸፉ ፖለቲከኞች አይደሉም። በቋንቋ ፌዴራልዝም ላይ አስተዳደሩን የገነባው የሕወሓት ኢሕአዴግ አገዛዝ ዜጎች ያልመከሩበትን ያላጸደቁትን ሕግ በጉልበት ዜጎች ላይ ይተረጉመዋል። ሕገመንግስቱን በተግባር የምናውለው ለመገንጠል ነው የሚሉት ሕወሓቶች ሃገሪቱ ላይ አደጋ ደቅነዋል። ከፀደቀ ጀምሮ አቧራ እየጠጣ ያለውና በተግባር ላይ ያልዋለው ሕገመንግስትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ያሉ ሕጎች ሁሉ ከሕዝብ እውቅና ውጪ የተሰሩና ዜጎችን ያገለሉ የዜጎችን በደል ያበዙ አደገኛ መንግስታዊ ሽብሮች ናቸው። በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ተረጋግጦ ማየት የማይሻ የለም። ወሬዎች ወደ ተግባር ትግል ተቀይረው ሃገራችንን እናድን።

«
Next
Newer Post
»
Previous
Older Post

No comments:

Leave a Reply