ወቅቱ 1973 ዓ.ም ነበር፡፡ አገሪቱ ከተለያዩ የውስጥና የውጪ ኃይሎች ጋር ጦርነት ውስጥ የገባችበት ጊዜ፤ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ልጆቻቸውን ያለ አሳዳጊ ጥለው በየጦር ሜዳው የወደቁበት ወቅት፤ አሳዳጊና ተንከባካቢ ያጡት ህፃናት በየጎዳናው መውደቃቸው ያሳሰበው የደርግ መንግስት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በነበሩት መንግስቱ ኃይለማርያም ልዩ ትዕዛዝ የአብዮታዊት ኢትዮጵያ ህፃናት አምባ ተቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
አምባው ገና ከተወለዱ ህፃናት ጀምሮ በተለያዩ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ህፃናትን ተቀብሎ እያሳደገ ያስተምርና ዕድሜያቸው 18 ዓመት ሞልቷቸው አምባውን ለቀው በሚወጡ ጊዜ በስነ ምግባር የታነፁ እንዲሆኑና በማህበራዊ ህይወታቸውም የመገለል ስሜት እንዳያድርባቸው ልዩ የምክር አገልግሎት ይሰጣቸው እንደነበር የቀድሞው የአምባው ልጆች ያስታውሳሉ፡፡ “አምባው አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ማግኘት ያለበትን ደስታና ፍቅር አግኝተን ያለፍንበትና ለህይወታችን መሰረት የሆነን ዕውቀት የቀሰምንበት ቦታ ነው፡፡ ራሳችንን በአግባቡ መግለፅ የምንችል፣ በራሳችን የምንተማመን ልጆች ሆነን እንድናድግ ያደረገን አምባው ነው” መቅደስ ተመስገን (10 ዓመታትን በአምባው ያሳለፈች)
በንጉሱ ዘመን ልጆችን መንግስት በሃላፊነት ወስዶ ያሳድግ እንደነበርም ይታወቃል።
የአምባው ህፃናት መሳጭና መልእክት አዘል በሆኑት ህብረ ዝማሬዎቻቸው በእጅጉ ይታወቃሉ። በተለይም “ፀሐዬ ደመቀች” ን በልጅነቱ ያላዳመጠና አብሮ ያልዘመረ ይኖራል ማለት ይከብዳል። በ1989 ዓ.ም ህፃናት አምባው በአዋጅ እንዲፈርስ ከተደነገገ በኋላ ወያኔ የሚታወቅበትን ኢ-ሰብዓዊነት የሆነ በትሩን በህፃናቱ ላይ አሳረፈ። ከሁሉ የሚያሳዝነው ግን ክረምቱን ለማሳለፍ በአምባው ውስጥ በቆዩት ልጆች ላይ የተፈፀመው ድርጊት ነው፡፡ ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ የሆኑትን ልጆችን “የደርግ ልጆች” በሚል በምሽት ዝዋይ ከተማ ወስደው ሜዳ ላይ በተኗቸው፡፡ በዚህም የተነሳ አብዛኞቹ ለሞት፣ ለስደትና ለቡና ቤት ህይወት ተዳረጉ፡፡ ህፃናት አምባው በጦርነትና በተፈጥሮአዊ አደጋዎች ወላጆቻቸውን ያጡ፤ አሳዳጊና ተንከባካቢ የሌላቸው ልጆች እንዲያድጉበት ታስቦ የተሰራና ህፃናት በስነ ምግባርና በትምህርት የሚታነጹበት ስፍራ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ይዘት አልነበረውም፡፡ ወያኔዎች ወላጅ አልባ ሕፃናት ጎዳና እንዳይወጡ እንደ ሕፃናት አምባ ዓይነት መስርተው ከማሳደግ ይልቅ ለአንድ ሕፃን እስከ 25000 ዶላር እየተቀበሉ በጉዲፈቻ ስም ለአሜሪካ እና አውሮፓ ይቸበችባሉ…
እድሜ ይስጠን………
ምንጭ ጎልጉል የድህረገፅ ጋዜጣ
Ethiopian News
Movies
Drama
Sport
Opinion
History
Home
»
»Unlabelled
» ሕፃናት ዓምባ “ፀሐዬ ደመቀች…” (እሸቱ ታደሰ)
Gulecha News's Author
- Eshe Man Tade
- Each one of us must take personal responsibility to speak up, stand up and defends for each other regardless of ethnicity, religion or any other.
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Popular Posts
-
By - Felix Horne (Senior Researcher, Horn of Africa) “Wako” fled Ethiopia for Kenya in 2012, after his release from prison. He had been lock...
-
የበረሃው ንድፈ-ሀሳብና የኢሕአዴግ መንግስታዊ ቆመጥ የአማራ ብሔር ጉዳይ ከግንቦት 1983 ዓ.ም በፊት ያለቀ ጉዳይ ነው፡፡ የአማራ ብሔር ተወላጆችን አከራካሪ ለመስበርና ሁለንተናዊ አቅማቸውን (በተለይም የኢኮኖሚያዊና የፖለ...
Author
- Eshe Man Tade
- Each one of us must take personal responsibility to speak up, stand up and defends for each other regardless of ethnicity, religion or any other.
Comments
Labels
AFRI Aviation Plc
Agence France-Presse
Amharic
Benishangul-Gumuz
Breaking News
Drama
Entertainment
Eritrea
ESAT
Ethio-Eritrea
Ethiopia
Ethiopian News
Gobena Mikael Imru
Grand Renaissance Dam
Health
History
Interviews
Kenyan News
Movies
Music video
News
Opinion
Sport
Video Gallery
World News
ህይወት እና ፍልስፍና
ሌሊሳ ግርማ
ሐብታሙ አያሌው
ሙሉቀን ተስፋው
ስዩም ተሾመ
ቢቢሲ አማርኛ
ባሕር ዳር
ነፃ አስተያየት
አማርኛ
አሰቦት ገዳም
አሳዬ ደርቤ
አቶ ታዬ ደንደኣ
አቻምየለህ ታምሩ
ኢትዮጵያ
ኤርትራ
ኦብነግ
ከበደ ሚካኤል (ዶ/ር)
ከአድማሱ ባሻገር
ኮ/ል አብዲሳ አጋ
ወልቃይት
ዜና
የኔስ ሔዋን
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው
ጋዜጠኛ ፍስሀ ተገኝ
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ግጥም
ጎበና ሚካኤል እምሩ ኃይለሥላሴ
No comments: