Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

» »Unlabelled » እኛኮ ጉዶች ነን…የጉድ ታሪክ ቱጃሮች… (ግርማ በቀለ)


‹‹ ነቢይ በአገሩ አይከበርም ›› ብለን ደምድመን ተነስተን  ‹‹ነቢዮቻችን ›› ከማዋረድ አልፈን ከመቅበር የማንመለስ አገር ወዳዶች፤
ከእኛ አልፈው ለዓለም የበቁና ዓለም የመሰከረላቸውን ጠበብቶቻችንን  የማናደንቅ ይልቁንም የምናዋርድ የክብር ጠበቆች፤
የፍቅርና መከባበር፣ የአብሮነትና መተሳሰብ መምህራን --- ዘር ቆጣሪ የ‹‹መገንጠል›› ታጋዮች፤ በአንድ የማንቆም የአንድነት ሰባኪ ፖለቲከኞች፣ የ‹‹ቅድመ ሃይማኖት ባለታሪክነት››  ሞጋቾች --የእምነት ቤት ዘራፊዎች፣ የፖለቲካ ተልዕኮ ግብረ ኃይል ‹‹የሃማኖት አባት›› ተከታዮች፤ ከቃል አልፈን በተግባር የማንገኝ፣‹‹ ሀፍረተ ቢስ ››ነጻ  አውጪዎች፣ በላስቲክ ቤት በሚኖር ወገን መሃል ፎቅና ‹‹መቃብር ቤት›› ለመገንባት የምንሰርቅ  ሩህሩህ ‹‹ወገን ወዳዶች››፤ ከተራበ ወገን ጉሮሮ የምንመነትፍ የሙስና ተዋጊዎች፤ ወንድማችን የምንገል /የምንገዳደል/ የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾች፤ የጥቁር ህዝብ  የነጻነት ተምሳሌት ሆኖ በዓለም ይመዝገብልን ብለን ልንጠይቅ የሚገባንን ሃውልት ይፍረስልን የምንል፤ የነጻነት ተሟጋቾች፤ በዲፕሎማሲ ትግልና ፣ቦታ ሰጥተው  ባቋቋሙት አፍሪካ ኅብረት  ፊት  …. የሌላ አገር መሪ ሃውልት የምናቆም---   ምርጥ‹‹ዲፕሎማቶች›› ፣ ሰላም አስከባሪ የአፍሪካ ጠበቆች፤
ለአገራቸው በጽናት የቆሙ የኃይማኖት አባት  መታሰቢያ የቆመ ሃውልት ሲፈርስ ፣ ለፖለቲከኛ  የኃይማኖት አባት ሃውልት ሲቆም ዝም የምንል ኃይማኖተኞች፤ ራሳችን መነጋገር ሳንችል መንግስትን አነጋግረን የምንል የፖለቲካ ጠበብቶች፤ ‹‹መሪዎቻችን ››አሳስረን እንቅልፍ የሚወስደን ‹‹ታጋዮች››፤ ወጣቱ በስደት ሲያልቅ በቪ8 ለቅሶ ደራሽ የአገር መሪዎች፣ አሹቅ እንዲበላ መካሪ አርቲስቶች፤
ድንጋይ ጠራቢ ‹‹መሃንዲስ ›› አስመራቂ የዕውቀት ማስፋፊያ ዩኒቨርስቲ ገንቢዎች፤ ስለ አገር ፍቅር ብንናገር ማይታክተን በ‹‹ስደት›› የምንኮራ  አገር ወዳድ ዲያስፖራዎች፤ መጽሃፍ በኪሎ የምንሸጥ ሲያልፍም የምናቃጥል ---- የቅርስና  ታሪክ ተቆሪቋሪዎች፤ ለወጣቱ/ልጆቻችን/  ለስርቆት ‹‹ሥራ አዋቂ ››ብለን የምናስተምር የትውልድ ባለአደራዎች…፤ በትናንት ቦታችን የማንገኝ መከፋፈል፣መካካድና መፈራረጅ ጌጥ የሆነን የጽናትና መተማመን የፖለቲካ ተንታኞች፤ የኃሳብ ነጻነት፣ መከባበርና መወያየት ሰባኪ --- የፌስ ቡክ  ተሳዳቢ ‹‹አርበኞች››፤ የሽምግልናና ዕርቅ ባለታሪክ -- ሃይል/ጠመንጃ/ አምላኪ ዲሞክራቶች፤ በስልጣኔ ፈር ቀዳጅነትና የጠቢባን አገርነት  የምንኮራ -- ወንድም ገዳይ ‹‹ጀግኖች››… እኛ ምን ያልሆነው አለና እንዴት ዘርዝሬ ልጨርሰው፣ የእኛ ጉድና የጉድ ታሪክ ሃብታችን ተዝቆ አያልቅምና የተሳሳተውን አርማችሁ የእናንተንም ትዝብት ጨምሩበትና ‹‹የጉድ መዝገባችን ›› ይዳብር፡፡ እስከመቼ  የነበርንበትንና ያለንበትን ለመመዘን - ጆሮኣችንን የደፈንን አድማጮች፣ ዓይናችንን የዘጋን ተመልካቾች፣ አዕምሮኣችንን የቆለፍን ተማሪዎች….. ሆነን እንቀጥላለን ? እናሰላስለው፡፡

የእኔ መልስ -- ይህ  የጉድ ታሪካችን ተቀልብሶ፣የጠፋብን ሚዛን ተመልሶ እምዬ ኢትዮጵያ በዓለም ፊት በክብር እንደምትጠራ፣‹‹ነቢይ ›› እንደሚከበርባትና ጊዜውም እንደተቃረበ ቅንጣት አልጠራጠርም፤ በቅዱሳን መጻህፍት የተጻፈው ቃልኪዳን ይፈጸም ዘንድ ፡፡
በቸር ያገኛኘን//

«
Next
Newer Post
»
Previous
Older Post

No comments:

Leave a Reply