በወያኔ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ያላደገ ነገር እንደሌለና (ኪሳቸውን ጨምሮ) ይሄንኑ እድገት ወደፊትም እንደሚያስቀጥሉ ሲለፈልፉ ለሰማ በጣም ሊያስደምም እንደሚችል ግልፅ ነው። እውነትም ነው¡¡
© የጎዳና ተዳዳሪዎች በዝተዋል
© የጫት ቤቶች እጅግ በጣም ጨምረዋል
© በጉዲፈቻ ስም ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ህፃናት ቁጥር አይሏል (ሰኔ 25/2012 ቢቢሲ በድህረ ገፁ ላይ አንደዘገበው ኢትዮጵያ በአመት ከ5ሺህ በላይ ሕፃናት በማደጎነት ወደ ተለያዩ ሃገሮች ትልካለች)
© በእግር፣ በባህርና በተለያዩ መንገዶች የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን በርክተዋል
© ጉቦ፣ ሙስናና ዝርፊያ በአይነትም በብዛትም ተመንድገዋል ለዚያውም በመንግስት ደረጃ………
ለአብነት ያህል ይህን ልጥቀስ እንጂ ብዙ እድገቶችን መጥቀስ ይቻላል። ይህንን እውነት ሳስብ ካለፈው አሰቃቂ ወቅት ይልቅ መጪው ጊዜ እጅግ በጣም አስፈሪ የሚሆን ይመስለኛል።
እንግዲህ መፍትሔው በእጃችን ነው ይኸውም "በአንድነት አንድ መሆን" ብቻ!!!
No comments: