Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

» »Unlabelled » ታላላቅ ሰዎች ከመሞቻቸው በፊት የተናገሩት


“ይቅርታ አድርግልኝ ጌታዬ፤ ሆን ብዬ ያደረግሁት አይደለም”
ንግስት ሜሪ አንቶይኔቴ
(የሰቃይዋን እግር በስህተት ረግጣ የተናገረችው)

· “እኖራለሁ!”
የሮማ ንጉስ
(በራሱ ወታደሮች ከመገደሉ በፊት)

“ህመም ይሰማኛል፤ ሀኪሞቹን ጥሯቸው”
ማኦ ዜዶንግ
(የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ መሪ)

“የተጎዳ ሰው አለ?”
ሮበርት ኤፍ.ኬኔዲ (የአሜሪካ ፕሬዘዳንት)
(በጥይት ከተመቱ በኋላ ኮማ ውስጥ ከመግባታቸው ጥቂት ሰኮንዶች በፊት ሚስታቸውን የጠየቁት)

“አትጨነቅ፤ ዘና በል!”
ራጂቭ ጋንዲ (የህንድ ጠ/ሚኒስትር)
(በአጥፍቶ ጠፊ ከመገደላቸው ጥቂት ደቂዎች በፊት ለፀጥታ ሰራተኛቸው ያሉት)

“ኢየሱስ እወድሀለሁ! ፤ ኢየሱስ፤ እወድሃለሁ!”
ማዘር ቴሬሳ
(ህንዳዊት መነኩሲት፣ በጎ አድራጊ)

“በደንብ አውቅሻለሁ እንጂ! ፍቅሬ ነሽ፤ እወድሻለሁ”
ጆን ዋይኔ
(ለሚስቱ የተናገረው)

“ኦህ ዋው! ኦህ ዋው! ኦህ ዋው!”
ስቲቭ ጆብስ
(የአፕል ኮምፒዩተር መሥራች)

“እማማ፤ እቃዎቼን እሸክፍና ከዚህ ቤት እወጣለሁ፡፡ አባባ ጠልቶኛል፤ ስለዚህ ተመልሼ አልመጣም”
ማርቪን ጌይ
(በአባቱ ከመገደሉ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ያለው)

“የፍሎሪዳ ውሃዬን”
ሉሲሌ ቦል
(የምትፈልገው ነገር ካለ ተጠይቃ የመለሰችው)

“ለምን ታለቅሳላችሁ? ለዝንተ ዓለም የምኖር መስሏችሁ ነበር?”
ሉዊስ 14ኛ
(የፈረንሳይ ንጉስ)

“መሞቴ ነው ወይስ ልደቴ ነው?”
ናንሲ አስቶር
(ስትነቃ በቤተሰቦቿ መከበቧን አይታ የተናገረችው)

“ኦህ … አታልቅሱ - ጥሩ ልጆች ሁኑ፤ እናም ሁላችንም በገነት እንገናኛለን፡፡”
አንድሪው ጃክሰን
(የአሜሪካ 7ኛው ፕሬዚዳንት)

«
Next
Newer Post
»
Previous
Older Post

No comments:

Leave a Reply