Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

ESAT

Ethiopian News

Movies

Drama

Sport

Opinion

History

» » » ቦርጭም ከሆነ ይቆያል ፅንስም ከሆነ ይታያል!! (አሌክስ አብርሃም)

ሰላም ሰላም ጓዶች እንዴት ናችሁ … እኔ እንደተለመደውና ከተለመደውም በላይ እጅግ በጣም ሰላም  ነኝ !! በርካታ የፅሁፍ መልእክቶች ይታዩኛል ገና አላነበብኳቸውም ! ስለላካችሁልኝ ግን የምስጋና ቀብዳችሁን ተቀበሉ ! ያው አጋጣሚ ተገጣጥሞ መጥፋቴን ከብዙ ነገሮች ጋር አያይዛችሁ ብታስቡትም ጉዳዩ ወዲህ ነው …ሹክ ልበላችሁ (((ሌላ ዙረት ላይ ነኝ)))) ሃሃ 

‹‹ቧ ሙናባክ ነው እዚህ ህዝብና መንግስት የሰጠህን የፌስቡክ ገፅ ትተህ የሙትዞረው›› የሚል ጥያቄ ቢነሳ ተገቢ ነው ! ህይዎት በየመቶ ሜትሯ ግራሞት የሚጭሩ ነገራ ነገሮቿን እያስቀመጠች አንድ እርምጃ በተራመዳችሁ ቁጥር ሌላ ተራመዱ ተራመዱ የሚል ጉዳይ ከፊታችሁ እየተደቀነ እንኳን በውናችሁ በህልማችሁም አስባችሁት የማታውቁት ቦታ ትከሰታላችሁ ልክ እንደዚህ እንዳሁኑ . . .

አሁን ዙረቴ ካዞረብኝ ከስድስት በላይ አገራት ስዊዲን በምትባል ሃብታም አገር  ከትሜ ኢትዮጲያን በአዲስ አመት ውበቷ ከሩቅ እያሰብኳት ነው …. አለ አይደል እድሜውን ቢሰጠን የዛሬስ አመት የት እንሆን አይነት ጉጉት …. ለማንኛውም የእውነት ይችን እንኳን መክተቢያ ጊዜም አልነበረኝም  እኔ ደግሞ ጥሎብኝ ለስታተስ ያህል መሞነጫጨር… አልወድም ! የተሰማኝን በተሰማኝ ልክ ሰፋ ቦርቀቅ አድርጌ ስጨዋወት ነው ደስ የሚለኝ …ቁጥ ቁጥ ምን ያደርጋል !  ይሁን ግዴለም የት ይሄድብናል ! እና ዛሬ እንደምንም የተከሰትኩት በሁለት ምክንያት ነው ….አንድ ለመላ ወዳጆቸ መልካም አዲስ አመት ለማለት ነው ….ይሄው አልኳችሁ ቆይ ምኞቴን እንዲህ ልግለፀው ....

‹‹ላለፉት 26 ዓመታት የመንግስት  ብቻ የነበረው የኢትዮጲያ መልካም አዲስ አመት የመላው ኢትዮጲያዊ እንዲሆን እንመኛለን›› አንድ ሰው አሚን ይበል !

ሁለተኛ …. ብዘገይም ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እንዲሉ ከእኔ ከባለቤቱ አፍ ትሰሙት ዘንዳ ….((((( በኮማንድ ፖስቱ አዋጅ ምክንያት))  ዘግይቶ የነበረው መፅሃፌ ታትሞ ገበያ ላይ ውሏል ! ‹‹ ቦርጭም ከሆነ ይቆያል ፅንስም ከሆነ ይታያል ›› እንዲሉ ፅንስ ነበርና ጊዜውን ጠብቆ ተወልዷል!  ልጅህን እቀፍ  ላላችሁ ተቀብለናል!! (በሉ ደግሞ ይቀበላል ብላችሁ ህፃን አምጥታችሁ የአንተ ነው እንዳትሉ)ሂ !
 
  
ሁሉን ነገር ከአመት በፊት ጨራርሸ ማተሚያ ቤት ቁሞ ቀርቶ  ነበር !  አከፋፋዩን  ደውየ እህ መፅሃፌ ታተመ አሉ አመሰግናለሁ ስለው ‹‹ እንዴ አሌክስየ በመጀመሪያው ቀን  ሁሉም ኮፒ ወደማለቁ ተቃርቧልኮ›› የሚል መልእክቱን አድርሶኛል ! እንግዲህ ምን እንላለን  ‹‹አንፈርስም አንታደስም››  እነሆ ከማለት ውጭ ! ከብዙ ምስጋናና ፍቅር ጋር ወደፊት !! እህሳ ወደፊት ጉዳያችን እንዴት ነው የሚለው ጥያቄ አይቀርም መቸም ….ይችን እያነበባችሁ ቆዩኝ ከብዙ ብዙ የጉብኝት ታሪኮች ጋር አለምን ባየኋት ልክ ላሳያችሁ አከሰታለሁ … ወገኖቸ ጎግል ላይ ያማታገኙት ጉዳይ በዚህ አለ … ከትንሽ ጊዜ በኋላ ከአሜሪካ ተነስተን  እስከ ...ዙረቴ መዳረሻ  የማወራላችሁ ብዙ ነገር አለ … ኢ ን ሻ አ ላ ህ  እንፅፋለን !!

መልካም አዲስ አመት !!

«
Next
Newer Post
»
Previous
Older Post

No comments:

Leave a Reply